በአዲሱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግመታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ 210.7 ከፍ ብሏል - የገንዘብ ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

በአዲሱ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግመታ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ወደ 210.7 ከፍ ብሏል - የገንዘብ ሚኒስትር

በዚህም ኢኮኖሚው ከፍ ያለ ዕድገት በማስመዝገብ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ሦስተኛ ግዙፍ ኢኮኖሚ ሆኖ መሰለፉን የገንዘብ ሚኒስትር ፍፁም አስፋው (ዶ/ር) የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ወቅታዊ የማድረግ ሥራ (GDP Rebasing) ውጤት ይፋ ባደረጉበት ወቅት አስታውቀዋል።

ይፋ በሆነው ውጤት መሠረት ፦

የ2017 በጀት ዓመት አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ወደ 24.03 ትርሊዮን ብር (201.42 ቢሊዮን ዶላር) ከፍ ብሏል፡፡

በ2018 በጀት ዓመት በተመዘገበው ዕድገት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ 31.86 ትርሊዮን ብር (210.7 ቢሊዮን ዶላር) ደርሷል፡፡

ከኢኮኖሚ መዋቅር አንፃር ፦

አገልግሎት ዘርፍ 35.91 በመቶ

ግብርና 31.57 በመቶ እንዲሁም

ኢንዱስትሪ 30.20 በመቶ ድርሻ ይዘዋል፡፡

ይህ አዲስ የሀገር ውስጥ ምርት ግመታ አሰላል፣ በሀገር ውስጥ ባለሙያዎች የተከናወነና ሙሉ በሙሉ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን የጠበቀ እንደሆነ ዶ/ር ፍፁም መጠቆማቸውን የብሔራዊ የስትራቴጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0