"ሩሲያ እጅግ ከፍተኛ አቅም አላት"፦ የዳያስፖራ መሪ ስለ አፍሪካውያን የቀጣይ እድሎች የሰጡት አስተያየት

ሰብስክራይብ

"ሩሲያ እጅግ ከፍተኛ አቅም አላት"፦ የዳያስፖራ መሪ ስለ አፍሪካውያን የቀጣይ እድሎች የሰጡት አስተያየት

በሩሲያ የሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራ ተወካዮች ከታሪካዊ ሀገራቸው ጋር ያላቸውን ትስስር አጠናክረው ከመጠበቅ ጎን ለጎን በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ በንቃት ሊሳተፉ እና ሊቀናጁ እንደሚገባ በሩሲያ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ዶ/ር ክንፉ ታፈሰ ዘነበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ባለሙያው አክለውም በአፍሪካ የሩሲያ ትምህርት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው እና በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች የመግቢያ ቦታዎች ላይ አከራካሪ እና ከፍተኛ ውድድር እንደሚደረግ ጠቁመው፤ በሩሲያ የሚማሩ የአፍሪካውያን ተማሪዎችን ቁጥር አሁን ካለበት 40 ሺህ ገደማ ወደ 700 ሺህ ማደግ እንዳለበት ሀሳብ አቅርበዋል።

"ሩሲያ ሰፊ እና ባለሀብት ሀገር ስትሆን በሀገሪቱ ውስጥ የሚሠሩ ባለሙያዎችም ያስፈልጓታል። ይህንን ተቃርኖ የሁለቱን አካላት ፍላጎት በሚያጣጥም መልኩ ማመጣጠን ይገባል።"

በቴክኖሎጂ፣ በፈጠራ ፣ በግንባታ እና በሌሎች ዘርፎች ሰፊ እድሎች መኖራቸውን የጠቆሙት ዶክተር ኪንፉ፤ የሩሲያን የሙያ ልምድ እና እውቀት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ይበልጥ ማጋራት እንደሚያስፈልግ አስምረውበታል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0