ሞስኮ ለውይይት ዝግጁ ብትሆንም ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር በስልክ ለመነጋገር የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አደረጉ

© telegram sputnik_ethiopiaሞስኮ ለውይይት ዝግጁ ብትሆንም ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር በስልክ ለመነጋገር የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አደረጉ
ሞስኮ ለውይይት ዝግጁ ብትሆንም ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር በስልክ ለመነጋገር የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አደረጉ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 04.11.2026
ሰብስክራይብ

ሞስኮ ለውይይት ዝግጁ ብትሆንም ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር በስልክ ለመነጋገር የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አደረጉ

ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር በስልክ ደረጃ የሚደረጉ ድርድሮችን "ትርጉም የለሽ" ሲሉ ውድቅ ያደረጉ ሲሆን፤ ሞስኮ የስልክ ጥሪውን በአካል ከሚደረግ ቀጥታ ውይይት ማምለጫ ምክንያት ልታደርገው ትችላለች ሲሉ ተናግረዋል።

"በስልክ የምንነጋገር ከሆነ ሩሲያ ዳግመኛ ላለመገናኘት እንደ መልካም አጋጣሚ ትጠቀምበታለች" ሲሉ ዘለንስኪ ከጀርመኑ መራኄ-መንግሥት ፍሬድሪክ ሜርዝ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለድርድር ወደ ሞስኮ ለመጓዝ የሚያስችለውን ሀሳብ ዳግም ውድቅ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ "ወደ ሞስኮ የሚደረግ ጉዞን ማንም ሊደግፈው አይችልም" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የክሬምሊን ረዳት ዩሪ ኡሻኮቭ፣ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዘለንስኪ ጋር ውይይት የማድረግን ሀሳብ ተቃውመው እንደማያውቁ ቀደም ሲል ተናግረው ነበር፡፡ በተጨማሪም የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ዘለንስኪ ከፑቲን ጋር ለመገናኘት ወደ ሞስኮ ቢመጡ ደስ እንደሚላቸው እና አስፈላጊው ሁሉ የደህንነት ዋስትና በሩሲያ እንደሚሰጣቸው ማረጋገጣቸው ይታወሳል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0