ዋና ግባችን እስከ 2030 ከአፍሪካ ጋር ያለንን የንግድ ልውውጥ 50 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ ነው - የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለሥልጣን

ሰብስክራይብ

ዋና ግባችን እስከ 2030 ከአፍሪካ ጋር ያለንን የንግድ ልውውጥ 50 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ ነው - የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለሥልጣን

ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር ለማስፋፋት አቅዳ እየሰራች መሆኗን የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባለሥልጣን ፓቬል ካልሚቼክ እ.ኤ.አ እስከ 2030 የሚዘልቀውን የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር የወደፊት ተስፋዎች አስመልክቶ በስፑትኒክ የፕሬስ ማዕከል ከተካሄደ የምክክር መድረክ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

ከቃለ-መጠይቁ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

በጉባኤው ወቅት የመንግስታት መካከል ኮሚሽኖችን ለማቋቋም የሚያስችሉ አምስት አዳዲስ ስምምነቶች የተፈረሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ከኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ከኬንያ እና ከደቡብ ሱዳን ጋር የተደረጉት ይገኙበታል።

ከአፍሪካ የሚገቡ ምርቶችን ማሳደግ ቀዳሚ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ ሲሆን፤ የግብርና ፕሮጀክቶች አስቀድሞም የኢንቨስትመንት ዘርፉን ሳቢ ስላደረጉት የመጀመሪያዎቹ የገቢ ምርት ጭነቶች መጀመራቸው ተገልጻል።

የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ማክሲም ሬሼትኒኮቭ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ተወካዮች ጋር በመገናኘት በጋራ የድርጊት መርሃ ግብር ዝግጅት ላይ ተመክሮባቸዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0