በአፍሪካ ሕብረት የተዘጋጀው የአፍሪካ የኃይል ደህንነት ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ ሆነ
20:54 03.11.2026 (የተሻሻለ: 21:04 03.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
በአፍሪካ ሕብረት የተዘጋጀው የአፍሪካ የኃይል ደህንነት ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ ሆነ
በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 36ኛው የአፍሪካ የውሃ ኃይል ሲምፖዚየም ላይ የአፍሪካ ሕብረት የኃይል ደህንነት ፖሊሲ ማዕቀፍ ይፋ ሆኗል።
የማዕቀፉ ዋና ዋና ነጥቦች፦
ዓላማ፦ በተስፋፉና ጥንካሬ ባላቸው ሥርዓቶች አማካኝነት በቂ፣ ዘላቂ፣ አስተማማኝ፣ ተመጣጣኝ እና ጥራት ያለው የኃይል አቅርቦት ለአህጉሩ ማረጋገጥ።
ትኩረት፦ እንደ ወረርሽኞች፣ ጦርነቶች፣ ጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች፣ የምጣኔ ኃብት ቀውሶች፣ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲሁም በኤሌክትሪክ፣ በባዮ-ኤነርጂ እና በነዳጅና ጋዝ ዘርፍ ያሉ መዋቅራዊ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ የተነደፈ ነው።
ስልታዊ አቀራረብ፦ በአፍሪካ ሀገራት ያለውን የኃይል አቅርቦት ደህንነት ለመቅረጽ፣ ለመለካት፣ ለመገምገም እና ለማስተዳደር ያስችላል።
የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክላቨር ጋቴቴ በማስጀመርያው ሥነ-ስርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር “የወንዝ ተፋሰሶችን የሚጋሩ ሀገራት የፖሊሲ ማዕቀፉን ፍሬያማ ለማድረግ የመረጃ ልውውጥን እና ቅንጅትን ማጠናከር አለባቸው።" ብለዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ የአፍሪካ ሀገራት ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት እና ተቋማትን ለማጠናከር በትኩረት መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
