የሩሲያ እና አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞችን መተግበር ጀምረዋል - የሩሲያ ኢንጂነሪንግ አካዳሚ ኃላፊ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ እና አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በጋራ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፕሮግራሞችን መተግበር ጀምረዋል - የሩሲያ ኢንጂነሪንግ አካዳሚ ኃላፊ

እ.ኤ.አ. እስከ 2030 የሚዘልቀውን የሩሲያ-አፍሪካ ትብብር የወደፊት ተስፋዎች አስመልክቶ ከተካሄደ የምክክር መድረክ ጎን ለጎን ከፓትሪስ ሉሙምባ ዩኒቨርሲቲ የተወከሉት ዩሪ ራዙምኒ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፤ እነዚህ ፕሮግራሞች ከሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥነ-ምግባር ጀምሮ በምህንድስና፣ በሮቦቲክስ እና በጠፈር ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ትግበራዎች ላይ የሚያተኩሩ ሲሆን በአፍሪካ ሀገራት ዘንድ ከፍተኛ ፍላጎት አሳድረዋል።

"ሁሉም ነገር በታቀደው መሠረት እና በስኬት እየሄደ ይገኛል" ሲሉ ራዙምኒ አረጋግጠዋል።

የአፍሪካውያን ተማሪዎችን የቀጣይ የሥራ እድል አስመልክተው አስተያየት የሰጡት ምሁሩ፤ ትምህርቱ "የአፍሪካ ተማሪዎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ" ታስቦ የተቃኘ መሆኑን እና "ለሀገራቸው ጠቃሚ የሆኑ" የምርምር ርዕሶችን በመምረጥ የሥራ እድል እንዲያገኙ እንደሚረዳቸው ጠቁመዋል።

"ተማሪዎቹ ገና ከመጀመሪያው ምዕራፍ ጀምሮ በሀገራቸው ሊፈልጓቸው ለሚችሉ የሥራ ቀጣሪዎች ዝግጁ ሆነው ነው የሚሰለጥኑት።"

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0