ኢትዮጵያ ውስጥ ለታላላቅ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የሚሆኑ 4 ተስፋ ሰጪ ስፍራዎች በጥናት ተለዩ
20:14 03.11.2026 (የተሻሻለ: 20:24 03.11.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ ውስጥ ለታላላቅ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የሚሆኑ 4 ተስፋ ሰጪ ስፍራዎች በጥናት ተለዩ
በ3ኛው የኢትዮጵያ የውሃና ኢነርጂ ሳምንት ላይ በቀረበ አዲስ ጥናት፤ ጎዴ፣ ሜጋ፣ አረርቲ እና ሰላ ድንጋይ ለታላላቅ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ስፍራዎች መሆናቸው ይፋ ሆኗል።
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲው ተመራማሪ የቀረበው ጥናት ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው የለያቸው ስፍራዎች፦
◻ጎዴ (ሶማሌ ክልል) እና ሜጋ (ኦሮሚያ)፦
⭕ ከፍተኛ የንፋስ ኃይል አቅም (በካሬ ሜትር 500–600 ዋት) አላቸው።
⭕ በጎዴ አንድ የ3 ሜጋ ዋት ተርባይን በዓመት 9,461 ሜጋ ዋት ሠዓት ማመንጨት እንደሚችል ተገምቷል።
⭕ በሜጋ ደግሞ 9,040 ሜጋ ዋት ሰዓት ማመንጨት ይቻላል።
◻ አረርቲ እና ሰላ ድንጋይ (አማራ ክልል)፦
ተስፋ ሰጪ አማራጮች እንደሆኑ ተለይተዋል።
⭕ አረርቲ ብቻዋን በዓመት 8,619 ሜጋ ዋት ሠዓት ማመንጨት የሚያስችል አቅም አላት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
