- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የአፍሪካ የወደፊት ኢንዱስትሪዎች፣ ከተስፋ ሰጪ አቅም ወደ አምራችነት ሽግግር

የአፍሪካ የወደፊት ኢንዱስትሪዎች፣ ከተስፋ ሰጪ አቅም ወደ አምራችነት ሽግግር
ሰብስክራይብ
እ.ኤ.አ. በ2024 ገደማ 83 በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ ሰራተኞች መደበኛ ባልሆነ የስራ ዘርፍ የተሰማሩ የነበሩ ሲሆን፤ ይህም የአህጉሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለምን በቂ፣ አስተማማኝ፣ አምራች እና ጥሩ ክፍያ የሚያስገኝ የስራ እድል መፍጠር እንዳልቻለ ያሳያል።
“የአፍሪካ አገሮች የረጅም ጊዜ እይታ ሊኖራቸው ይገባል። የአጭር ጊዜ ጥቅም ላይ ብቻ ማተኮር ለነገ የሚያስፈልጉንን ሃብቶች አሳልፈን እንድንሰጥ ያደርገናል። ከዚህ ይልቅ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን በመገንባት እና አጋርነትን በመፍጠር፣ ሀብታችን እዚሁ ከማዕድን ማውጫ እስከ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በየደረጃው እንዲለወጥ መስራት ይገባናል” ሲሉ ባንኬ አበጂሪን (ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።
እንደ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን 2024 (እ.ኤ.አ.) መረጃ 83 በመቶ የሚሆኑት የአፍሪካ ሰራተኞች መደበኛ ባልሆነ ዘርፍ የተሰማሩ በመሆናቸው አስተማማኝ ገቢ፣ ማህበራዊ ዋስትና እና ንግድን የማስፋፋት እድላቸው ተገድቧል። በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ከኮሚሽኑ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ኦፊሰር ባንኬ አበጂሪን (ዶ/ር) ጋር በመሆን አፍሪካ የስነ ህዝብ፣ የተፈጥሮ እና የቴክኖሎጂ አቅሟን ወደ ተጨባጭ አምራችነት የምትቀይርበትን መንገድ እንመረምራለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0