አፍሪካ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለሚከሰቱ ጦርነቶች መሣሪያውንም ሐሳቡን የሚያቀርቡት የቀደሞ ቅኝ ገዥ ምዕራባውያን ናቸው – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
አፍሪካ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች ለሚከሰቱ ጦርነቶች መሣሪያውንም ሐሳቡን የሚያቀርቡት የቀደሞ ቅኝ ገዥ ምዕራባውያን ናቸው – ኢትዮጵያዊ ባለሙያ
በባህል፣ በፊልም እና በትምህርት ሥርዓት ውስጥ የቅኝ ገዥ ምዕራባውያን አስተሳሰብና ዕይታ ጎልቶ እንዲታይ እየተደረገ መሆኑን አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የታሪክ ተመራማሪ እና ደራሲ ጥበቡ በለጠ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
ባለሙያው፣ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተከበረው የአፍሪካ ወጣቶች ቀን ጎን ለጎን ከስፑትኒክ አፍሪካ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ያነሷቸው ሌሎች ነጥቦች፦
የኢኮኖሚ ጥገኛነት እና ዕርዳታ
አፍሪካ በአዲሱ የግዛት ሥርዓት በከፍተኛ ሁኔታ ተወጥራለች፤ የአፍሪካ መንግሥታት በእርዳታ ላይ ብቻ እንዲመሠረቱ በመደረጉ፣ የምዕራባውያን ቅኝ ገዢዎች እጅና ኪስ (ኮሮጆ) እንዲጠባበቁ ተደርገዋል።
የባህል እና የአስተሳሰብ ቅኝ ግዛት
የቅኝ አገዛዝ አሁን ላይ በአካል ቀርቶ እንደገና በሰው አእምሮ ላይ እየተሠራበት ይገኛል ብለዋል።
ባለሙያው ራሳቸውን ጨምሮ ብዙዎች ለምርምርና ለትምህርት የሚሄዱት ወደ አውሮፓ ሀገራት መሆኑን እና ትምህርቱም የሚሰጠው በአውሮፓውያን ሥርዓት ላይ ተመስርቶ መሆኑን አንስተዋል።
አፍሪካን ማዕከል ያደረገ ትምህርት አስፈላጊነት
ባለሙያው እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያዊ ወይም አፍሪካዊ ሥርዓት የተከተለ፣ አፍሪካን ማዕከል ያደረገ የትምህርት ሥርዓት ሊኖር ይገባል።
አሁን ላይ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባሉ ተቋማት ውስጥ “የአፍሪካ ጥናቶች" መሰል ትምህርቶች ቢኖሩም፣ አሁንም በስፋት ሊሰራበት ይገባል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
