የሩሲያ እና አፍሪካ አጋርነት የሁለትዮሽ የጋራ መንገድ ነው - ናይጄሪያዊ ተወካይ

ሰብስክራይብ

የሩሲያ እና አፍሪካ አጋርነት የሁለትዮሽ የጋራ መንገድ ነው - ናይጄሪያዊ ተወካይ

በቅርቡ በሞስኮ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ የተሳተፉ አንድ ናይጄሪያዊ ተወካይ ለስፑትኒክ አፍሪካ እንደገለጹት፤ የአፍሪካ አኅጉር የተፈጥሮ ሀብቶች ለመጪው ዓለም አቀፋዊ ምኅዳር እጅግ አስፈላጊ ናቸው።

🟠 ኃያል አጋር፦ ሞስኮን የታላቅ መጪው ጊዜ አጋር ሲሉ የገለጿት ተወካዩ፣ በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ኃያላን ሀገራት አንዷ እንደመሆኗ መጠን ያሳየችውን የመቋቋም አቅም አድናቀዋል።

🟠 የጋራ ጥገኝነት፦ ሩሲያ ለራሷ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ድጋፍ ታገኝ ዘንድ አፍሪካ በእርግጥ እንደምታስፈልጋት ገልጸው፤ በተለይም የናይጄሪያን ሰፊ የማዕድን ሀብት እና ጠንካራ የሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አጉልተው አሳይተዋል።

🟠 ታላቅ ዕድል፦ ተወካዩ በማጠቃለያቸው ይህ ጉባኤ አፍሪካውያን ከሞስኮ ጋር ጠንካራ እና እርስ በርስ ጠቃሚ የሆነ የሥራ ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችላቸው ወሳኝ ዕድል እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0