5ኛው የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ አፍሪካ የጤና ሉዓላዊነቷን እንድታረጋግጥ የሚያግዝ ነው - ጤና ሚኒስትር

ሰብስክራይብ

5ኛው የአፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና ጉባኤ አፍሪካ የጤና ሉዓላዊነቷን እንድታረጋግጥ የሚያግዝ ነው - ጤና ሚኒስትር

ጉባኤው አፍሪካውያን ለጋራ የጤና ችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማፍለቅ የሚመክሩበት መድረክ እንደሚሆን የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ከኅዳር 14-18 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚያካሄደው ጉባኤ አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ መግለጻቸውን የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ዘግቧል፡፡

የአፍሪካ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዶክተር ጂያን ካሰያ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ጉባኤውን ለማካሄድ ያደረገችውን ዝግጅት የተሟላ እና ስኬታማ ሲሉ ያደነቁ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የጤና ስርዓቱን በዲጂታል ስርዓት ለማዘመን ለወሰዱት ተነሳሽነት እውቅና ሰጥተዋል።

  

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እና የአፍሪካ ሲዲሲ የጋራ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

▪ ከ114 ሀገራት የተውጣጡ ከ30 ሺህ በላይ አካላት በጉባኤው ላይ ለመሳተፍ ተመዝግበዋል፡፡

▪ ጉባኤው በተለይም ለኢቦላ ወረርሽኝ የተቀናጀ እና ሁሉን አቀፍ የሆነ ወጥ አፍሪካዊ ምላሽ ለመስጠት ያግዛል።

▪ መድረኩ ተመራማሪዎች፣ ምሁራን፣ የጤና ኃላፊዎች፣ ተቋማት፣ እና የጤና ዘርፍ ባለሃብቶችን በአንድ ያገናኛል።

▪ በጉባኤው ላይ ከ6000 ሥራዎች ውስጥ የተመረጡ 1000 ሳይንሳዊ የምርምር ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡

▪ ከ25 ሀገራት የተውጣጡ አካላት በ70 የጤና እና ተያያዥ ዘርፎች ዐውደ ርዕዮች ላይ ይሳተፋሉ።

▪ ኢትዮጵያ በተለይም በዲጂታል ጤና ዘርፍ ያስመዘገበችውን ውጤታማ ልምድ ለሌሎች ሀገራት ታካፍላለች።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0