ቱርክ በዩክሬን ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ድርድሮችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

© telegram sputnik_ethiopiaቱርክ በዩክሬን ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ድርድሮችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
ቱርክ በዩክሬን ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ድርድሮችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.11.2026
ሰብስክራይብ

ቱርክ በዩክሬን ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ድርድሮችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

"ቱርክ በዩክሬን ጉዳይ ላይ በሚደረጉ ውይይቶች በቴክኒክም ሆነ በከፍተኛ መሪዎች ደረጃ የሚደረጉ ድርድሮችለማስተናገድ ዝግጁ ነች። ይህ መልዕክት ዋሽንግተን የዩክሬንን ግጭት ለመፍታት እያደረገች ባለው ጥረት ማዕቀፍ ውስጥ ለሁኔታው ምላሽ እንዲሆን መልዕክቱ ለአሜሪካ ተላልፏል" ሲሉ በቱርክ መንግሥት ውስጥ የሚገኙ ምንጭ ለስፑትኒክ ገልጸዋል።

እንደ ምንጩ ገለጻ፤ አንካራ ለታቀዱት ድርድሮች ቅርፅ እና ደረጃ ተስማሚ የሚሆን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መድረክ ለማዘጋጀት ዝግጁነቷን አረጋግጣለች።

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ቀደም ሲል በዩክሬን ሰላም ዙሪያ የሚደረጉ ድርድሮችን በሦስትዮሽ መድረክ ማዕቀፍ ለማስቀጠል ሩሲያ ዝግጁ መሆኗን ማስታወቃቸው ይታወቃል። ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፤ ውይይቶቹ ዘላቂ የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ለሩሲያ እና ለዩክሬን የሚሰጡ የደህንነት ዋስትናዎችን ለመወሰን ያለመ ይሆናል።

ፑቲን፣ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች ሰፊውን የአውሮፓ የደህንነት መዋቅር ያካተተ መሆን እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0