የአፍሪካ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ከሩሲያ ዐበይት መንፈሳዊ ማዕከላት አንዱ የሆነውን ታሪካዊ ገዳም ጎበኙ

ሰብስክራይብ

የአፍሪካ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ከሩሲያ ዐበይት መንፈሳዊ ማዕከላት አንዱ የሆነውን ታሪካዊ ገዳም ጎበኙ

የአፍሪካ ኦርቶዶክስ ካህናት ልዑክ በሩሲያ ከሚገኙ ዋና ዋና የኦርቶዶክስ ገዳማት አንዱ እና በዩኔስኮ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውን 'ቅድስት ሥላሴ ሰርጊየስ ላቭራ' ገዳም መጎብኘቱን የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የአፍሪካ አኅጉረ ስብከት አስታውቋል።

ከሞስኮ አቅራቢያ በሰርጊዬቭ ፖሳድ የሚገኘው ይህ የዘመናት ታሪክ ያለው ገዳም የሩሲያ ኦርቶዶክስ ክርስትና ዋነኛ ማዕከል ነው።

በጉብኝቱ ወቅት ልዑኩ ቅዱሳት መካናትን እና ንዋያተ ቅድሳትን የጎበኘ ሲሆን በሞስኮ የሥነ-መልኮት አካዳሚ ተማሪዎች ጋር በመገናኘት በገዳሙ የሚገኙ ታሪካዊ የክርስቲያን ሥነ-ጥበብ ስብስቦችንም መመልከቱን አኅጉረ ስብከቱ ገልጿል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0