ብሪክስ አዲስ ዓለም አቀፍ የኃይል መዋቅርን በመምራት የአፍሪካን መፃኢ ዘመንን ያበራል - የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መሪ

ሰብስክራይብ

ብሪክስ አዲስ ዓለም አቀፍ የኃይል መዋቅርን በመምራት የአፍሪካን መፃኢ ዘመንን ያበራል - የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት መሪ

እ.ኤ.አ. በ2030 የአፍሪካ ሀገራት በቀን ከ11 ሚሊዮን በርሜል በላይ የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ አጠቃላይ አቅም ያመርታሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ወደ ብሪክስ መዋቅር መቀላቀል አህጉሪቱ እንደ ሩሲያ እና ቻይና ካሉ አባል ሀገራት የካበተ የኃይል ዘርፍ ልምድ እንድትቀስም ያስችላታል ሲሉ የአፍሪካ ኢነርጂ ምክር ቤት ሊቀመንበር ኤንጄ አዩክ በሞስኮ ከተካሄደው ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በብሪክስ የልማት ባንክ አዳዲስ የፋይናንስ አሠራሮች የሚደገፈው ይህ ስትራቴጂያዊ ትብብር የአፍሪካን ከፍተኛ የኃይል ፍላጎት በማሟላት ረገድ መሠረታዊ ለውጥ አምጪ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም አዩክ፤ የሩሲያ አነስተኛ ሞጁላር የኒውክሌር ማመንጫዎች ከ200 እስከ 300 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የሚጠይቁ እና ከ12 እስከ 24 ወራት ባለው ጊዜ ውስጥ ተተክለው ሥራ የሚጀምሩ በመሆናቸው ለአህጉሪቱ ወሳኝ የሆነውን የቋሚ መሠረታዊ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ማረጋገጥ እንደሚችሉ አፅንዖት ሰጥተው አብራርተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0