አፍሪካ ለተንሳፋፊ የኒውክሌር ማመንጫዎች ከፍተኛ አቅም አላት፤ ሩሲያ የተረጋገጠ ልምዷን ልታካፍል ትችላለች - የሮሳቶም ቀጣናዊ ተወካይ
አፍሪካ ለተንሳፋፊ የኒውክሌር ማመንጫዎች ከፍተኛ አቅም አላት፤ ሩሲያ የተረጋገጠ ልምዷን ልታካፍል ትችላለች - የሮሳቶም ቀጣናዊ ተወካይ
የአፍሪካ ረጅም የባሕር ዳርቻዎች ተንሳፋፊ የኒውክሌር የኃይል ማመንጫዎችን ለአህጉሪቱ ዝግጁና ፈጣን መፍትሔ የሚያደርጋቸው ሲሆን በተለይም ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከፍተኛ አቅም እንዳለው በሮሳቶም የመካከለኛው እና የደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ቢሮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሪያን ኮልየር ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
በሞስኮ በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ኮልየር እንደጠቆሙት፤ ተንሳፋፊ የኒውክሌር ማመንጫዎች እንደ ምድር ላይ ማዕከላት ከፍተኛ የመሠረተ ልማት ዝግጅት የማይጠይቁ በመሆናቸው የአፍሪካ ሀገራት ወደ ኒውክሌር ዘርፉ በፍጥነት እንዲቀላቀሉ ሊረዷቸው ይችላሉ።
ኃላፊው የሩሲያን የካበተ ልምድ በማስረጃነት የጠቀሱ ሲሆን በሰሜን ምሥራቅ ሩሲያ ላለፉት አራት ዓመታት ኤሌክትሪክ በማመንጨት ላይ የሚገኘውንና በዓለም ላይ ብቸኛው ሥራ ላይ ያለ ተንሳፋፊ የኒውክሌር ማመንጫ የሆነውን አካደሚክ ሎሞኖሶቭ አብነት አድርገው አቅርበዋል።
በተጨማሪም የሮሳቶም አካሄድ ቴክኖሎጂን ከማቅረብ ባለፈ የሰው ኃይል ልማትን፣ የኒውክሌር መሠረተ ልማትን፣ ጥገናን እና በፕሮጀክቱ ዕድሜ ልክ ሙሉ የነዳጅ አቅርቦትን የሚያካትት እንደሆነ አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
