አዲስ አበባ የ2026 የከተሞች ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ሽልማትን ማግኘቷ፣ ለኢትዮጵያ ታላቅ ኩራት ነው – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ሰብስክራይብ

አዲስ አበባ የ2026 የከተሞች ዘላቂ ልማት ዓለም አቀፍ ሽልማትን ማግኘቷ፣ ለኢትዮጵያ ታላቅ ኩራት ነው – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት

ጽሕፈት ቤቱ እንደገለጸው፣ መዲናዋ በተመድ የሰዎች ሰፈራ ፕሮግራም እና በቻይና የተዘጋጀውን የሸንሃይ ሽልማት ማሸነፏ፣ በከተማዋ የታየውን እድገት፣ ዘላቂ ልማትና ቀጣይነት ያለው ለውጥ የሚያረጋግጥ በመሆኑ "ለኢትዮጵያ ታላቅ ኩራት ነው" ብሏል፡፡

የጽሕፈት ቤቱ መግለጫ ዋና ዋና ነጥቦች፦

⭕ የእያንዳንዱን ከተማ ልዩ ታሪክ፣ ቅርስና ማንነት በመጠበቅ ዘመናዊ፣ አካታችና ዘላቂ ከተሞችን የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

⭕ የከተሜነት ባህልን ማሳደግ፣ ጥራት ያላቸው የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎችን መፍጠር እንዲሁም ከተሞቻችንን ለመኖርና ለመሥራት ምቹ ማድረግ ዋና ትኩረት ነው።

⭕ ከአዲስ አበባ ባሻገር ከሐረር እስከ ባሕር ዳር፣ ከሐዋሳ እስከ ጅማ፣ ከአርባ ምንጭ እስከ ድሬዳዋ ያሉ የኢትዮጵያ ከተሞች የዘላቂ ልማት ማሳያ እንዲሆኑ ይደረጋል።

በስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ የተቀረጸ ቪዲዮ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0