ኢትዮጵያ እስከ 2032 ዓ.ም ድረስ 1.78 ሚሊዮን የሙሉ ጊዜ ሠራተኞችን የሥራ ሠዓት በሙቀት መጨመር ምክንያት ልታጣ ትችላለች - ጥናት

© telegram sputnik_ethiopiaኢትዮጵያ እስከ 2032 ዓ
ኢትዮጵያ እስከ 2032 ዓ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢትዮጵያ እስከ 2032 ዓ.ም ድረስ 1.78 ሚሊዮን የሙሉ ጊዜ ሠራተኞችን የሥራ ሠዓት በሙቀት መጨመር ምክንያት ልታጣ ትችላለች - ጥናት

ዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ይፋ ባደረገው አዲስ ጥናት፣ በከፍተኛ የሥራ ቦታ ሙቀት ምክንያት ኢትዮጵያ፣ ጋና እና ሴኔጋል እስከ 2032 ድረስ በአጠቃላይ የ2.5 ሚሊዮን የሙሉ ጊዜ ሠራተኞችን የሥራ ሠዓት ሊያጡ እንደሚችሉ አመላክቷል።

የጥናቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

▪ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ጉዳት፦ ከሦስቱ ሀገራት እጅግ ከፍተኛውን ጉዳት የምታስተናግደው ኢትዮጵያ ስትሆን፣ 1.78 ሚሊዮን የሙሉ ጊዜ ሥራዎችን ታጣለች።

▪ የኢኮኖሚ ኪሳራ፦ በሙቀት መጨመር ምክንያት ሦስቱ ሀገራት በየዓመቱ በአጠቃላይ 67 ቢሊዮን ዶላር ያጣሉ። ከዚህ ውስጥ 33.3 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው የኢትዮጵያ የምርትና የኢኮኖሚ ኪሳራ ነው።

▪ ተጋላጭ ዘርፎች፦ ግብርና እና ግንባታ ዘርፎች ቀጥተኛ የፀሐይ ብርሃንና አካላዊ ጉልበት ስለሚጠይቁ በዋናነት ተጎጂ ናቸው። ማኑፋክቸሪንግ እና ትራንስፖርትም በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቂ ናቸው።

በኢትዮጵያ ባለፈው 2015 ዓ.ም ብቻ በሙቀት ምክንያት ከ1 ሚሊዮን በላይ የሙሉ ጊዜ የሥራ ሠዓት መጥፋቱን ጥናቱ ጠቅሷል።

በዚህም መንግሥታት እና አሠሪዎች የሥራ ሠዓት ማሻሻያ ማድረግ፣ በሥራ ቦታዎች ውስጥ የማረፊያ ስፍራዎችንና የውሃ አቅርቦት ማዘጋጀት፣ እንዲሁም ለማኅበራዊ ጥበቃ እና ለሥራ ቦታ ደህንነት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት በመፍትሔነት አስቀምጧል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0