ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ውይይት ላይ ውሳኔ የምትሰጠው ቅድመ ሁኔታዎቿ ሲሟሉ ብቻ ነው - አራግቺ

© telegram sputnik_ethiopiaኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ውይይት ላይ ውሳኔ የምትሰጠው ቅድመ ሁኔታዎቿ ሲሟሉ ብቻ ነው - አራግቺ
ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ውይይት ላይ ውሳኔ የምትሰጠው ቅድመ ሁኔታዎቿ ሲሟሉ ብቻ ነው - አራግቺ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 31.10.2026
ሰብስክራይብ

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በምታደርገው ውይይት ላይ ውሳኔ የምትሰጠው ቅድመ ሁኔታዎቿ ሲሟሉ ብቻ ነው - አራግቺ

"በአሁኑ ወቅት ከአሜሪካውያን ጋር የመገናኘት አስፈላጊነት አይታየንም። ቅድመ ሁኔታዎቻችን ግልጽ ናቸው፤ አሸማጋዮችም በእነዚህ ጉዳዮች ላይ ምክክራቸውን ቀጥለዋል" ሲሉ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ገልጸዋል።

አክለውም በአሁኑ ወቅት ኢራን ከአሜሪካ ባለሥልጣናት ጋር የመገናኘት ምንም ዓይነት ዕቅድ እንደሌላት ተናግረዋል።

ኳታር እና ፓኪስታን ኢራን ለድርድር ባስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች ላይ ምክክራቸውን ቀጥለውበታል ያሉት አራግቺ፤ አሸማጋዮቹ የኢራንን የኒውክሌር መዝገብ በተመለከተ ሀሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን ኢራንም እየገመገመቻቸው ይገኛል ብለዋል።

በአራግቺ መግለጫ መሠረት የኢራን ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

◼ የተጣሉ ማዕቀቦች እንዲነሱ፣

◼ በመካከለኛው ምስራቅ ውስጥ የአሜሪካ ጦር ኃይል እንዲቀነስ፣

◼ የነዳጅ ንግድ ማዕቀብ ማቃለያዎች ወደ ነበሩበት እንዲመለሱ እና

◼ በኳታር የሚገኘውን ጨምሮ የታገዱ የኢራን ሀብቶች እና ገንዘቦች በሙሉ እንዲለቀቁ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0