"ድምፃችን እየተሰማ አይደለም"፦ ፈረንሳይ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ አስተናገደች

ሰብስክራይብ

"ድምፃችን እየተሰማ አይደለም"፦ ፈረንሳይ በሦስት ሳምንታት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ የተቃውሞ ሰልፍ አስተናገደች

በተቃውሞው ላይ በተገኙት ተማሪዎች እና የሠራተኞች ማኅበራት የቀረቡት ቅሬታዎች ቀደሞ በነበሩበት ይገኛሉ፤ የኑሮ ውድነት፣ የፖሊስ ኃይል አጠቃቀም እና አጥጋቢ ያልሆኑ የሥራ እና የመማር ሁኔታዎች እንደሆኑ የስፑትኒክ አፍሪካ ባልደረባ ከስፍራው ዘግቧል።

"ምንም ዓይነት ድምፅ የማይሰማውን እና አንድ ምኞት ብቻ ያለውን እርሱም ጭቆና፣ ጭቆና እና ተጨማሪ ጭቆና የሆነውን ይህንን መንግሥት ለመኮነን እዚህ መገኘታችን አስፈላጊ ነው" ሲል ጆን የተባለ የየሎው ቬስት አባል ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግሯል።

"መንግሥት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጥያቄዎች ወይም የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄዎችን በበጎ አይመልስም" ሲል ሚሼል የተባለ ተማሪ አክሏል።

"ዛሬ እዚህ የተገኘነው በዋናነት የከፍተኛ ትምህርት ምደባ ሥርዓት እንዲሰረዝ የሚጠይቁትን እና በጥሩ ሁኔታ ለመማር የሚያስችሏቸውን ግብዓቶች የሚሹትን ተማሪዎቻችንን ለመደገፍ ነው። በተጨማሪም ለሕዝባችን፣ ለፈረንሳይ ብለን እዚህ ተገኝተናል። ከፍተኛ ደመወዝ እንዲከፈል እና ሕዝቡ ከግዥ አቅሙ ተጠቃሚ እንዲሆን እንጠይቃለን" ስትል ሳቢና የተባለች የካፌቴሪያ ሠራተኛ ገልጻለች።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0