እንግሊዝ ስለ ባሪያ ንግድ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ብትሆንም፤ ቀጥተኛ የካሳ ክፍያን ግን አልተቀበለችውም - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
18:34 31.10.2026 (የተሻሻለ: 18:44 31.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
እንግሊዝ ስለ ባሪያ ንግድ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ብትሆንም፤ ቀጥተኛ የካሳ ክፍያን ግን አልተቀበለችውም - ጠቅላይ ሚኒስትሩ
እንግሊዝ በአትላንቲክ ማዶ በነበረው የባሪያ ንግድ ውስጥ ለነበራት ሚና ይፋዊ የመንግሥት ይቅርታ ከመጠየቅ ወደኋላ እንደማትልና ድርጊቱም "የእነዚያን ሰዎች መብት የገፈፈ አሰቃቂ እና ዘግናኝ ጥሰት" እንደነበር ጠቅላይ ሚኒስትር አንዲ በርንሃም በሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ላይ ባወጡት ጽሑፍ ገልጸዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሑፍ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
▪ ቀጥተኛ የካሳ ክፍያ የለም፦ በርንሃም አሁን ያለው የእንግሊዝ ትውልድ "ላለፉት ታሪካዊ በደሎች ተጠያቂ ሊደረግ አይችልም" በሚል ምክንያት የገንዘብ ካሳ ክፍያ ጥያቄውን ተቃውመዋል።
▪ አማራጭ ድጋፍ፦ በካሳ ክፍያ ምትክ ለድሃ የኮመንዌልዝ ሀገራት የተሻለ የወለድ ምጣኔ እና የመክፈያ ጊዜ በመስጠት የዕዳ ሽግሽግ ማድረግን ለንደን እያጤነችበት ነው።
እ.ኤ.አ. በመጋቢት ወር የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ በጋና የቀረበውን እና የአትላንቲክ የባሪያ ንግድን የሚኮንነውን ውሳኔ ማጽደቁ ይታወቃል። ሆኖም እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ እና ጀርመንን ጨምሮ በርካታ የቀድሞ ኃያላን ቅኝ ገዥ ሀገራት ድምፀ-ተዓቅቡ አድርገዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
