የመደመር መንግሥት አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው – ዐቢይ አሕመድ
08:51 31.10.2026 (የተሻሻለ: 08:54 31.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የመደመር መንግሥት አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው – ዐቢይ አሕመድ
ሥልጠናው የመደመር ሥልጣኔ ታላቁን ስትራቴጂ በተግባር ለመተርጎም የሚያስችሉ ዕውቀቶችን፣ ክህሎቶችን እና ልምዶችን ለመቅሰም ያለመ መሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ገልጸዋል።
የሥልጠናው ዋና ዋና ዓላማዎችና የሚጠበቁ ውጤቶች፡-
🟠 አንድ የጋራ መግባቢያ መፍጠር፡ በአንድ ሰዋሰው በመግባባትና ሥነ-ምኅዳርን በሚገባ በመጠቀም አመራሩ በተመሳሳይ አቅጣጫ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ፤
🟠 ሕዝባዊ አደራን መወጣት፡ ሕዝብን ለተግባር ማነጽ፣ ለሕዝብ የተገባውን ቃል አከናውኖ ማጠናቀቅ እና ሀገርን በባለአደራነት መንፈስ መምራት፤
🟠 የመዋቅርና ደኅንነት ቅንጅት፡ ከታች እስከ ላይ ያለውን የመንግሥት መዋቅር ለሀገራዊ ዓላማ ማሳለጥ እና የሀገርን ደኅንነት ሁልጊዜም ማረጋገጥ፤
🟠 ጽኑ ሀገርና ተተኪ ትውልድ፡ ለምንምና ለማንም የማትበገር ጽኑ ሀገር መገንባት እንዲሁም ሀገራዊ ኃላፊነትን የሚረከብ ተተኪ ትውልድ ማፍራት፤
በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን፡፡” ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

1/6
© telegram sputnik_ethiopia

2/6
© telegram sputnik_ethiopia

3/6
© telegram sputnik_ethiopia

4/6
© telegram sputnik_ethiopia

5/6
© telegram sputnik_ethiopia

6/6
© telegram sputnik_ethiopia
1/6
© telegram sputnik_ethiopia
2/6
© telegram sputnik_ethiopia
3/6
© telegram sputnik_ethiopia
4/6
© telegram sputnik_ethiopia
5/6
© telegram sputnik_ethiopia
6/6
© telegram sputnik_ethiopia
