- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ከጉባኤ ባሻገር፣ የሩሲያና አፍሪካ ስኬቶች ምን ምን ናቸው?

ከጉባኤ ባሻገር፣ የሩሲያና አፍሪካ ስኬቶች ምን ምን ናቸው?
ሰብስክራይብ
እ.ኤ.አ. በ2025 የሩሲያና አፍሪካ የንግድ ልውውጥ ከ27 ቢሊዮን ዶላር በላይ የደረሰ ሲሆን፣ ሞስኮ ይህን መጠን ወደ 50 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግ አቅዳለች። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሦስተኛዋ ትልቋ የሩሲያ ማዳበሪያ አስመጪ ሆናለች።

ይህ ጉባኤ [ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ] ዓለም አቀፍ ውጥረት በነገሠበት ወቅት አፍሪካ እንደ ሩሲያ ያለ አስተማማኝ አጋር ያገኘችበት ልዩ መድረክ ነው። በተለይም በግብርና፣ በኃይልና በቴሌኮም ዘርፎች የሚደረገው የቴክኖሎጂ ሽግግርና የትምህርት ድጋፍ አህጉሪቱ የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ነፃነቷን እንድታረጋግጥ ያግዛታል” ሲሉ ዳዊት መዝገበ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

የአፍሪካ መሪዎች ለሦስተኛው የሩሲያና አፍሪካ ጉባኤ ሞስኮ የተሰበሰቡት ለስምምነት መፈራረም ብቻ አልነበረም፤ ይልቁንም አጋርነቱ ለወጣቶቻቸው ፋብሪካን፣ እርሻን፣ ትምህርትን፣ የኃይል ማመንጫዎችንና የሥራ ዕድልን ማምጣት ይችላሉ ወይ? የሚል ትልቅ ጥያቄ አንግበው ነበር። ባዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ታዲያ ሁለቱ አካላት ከዚህ ጉባኤ ምን አተረፉ ስንል በዲላ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች መምህር እና ተመራማሪ ከሆኑት እንግዳችን ዳዊት መዘገበ (ዶ/ር) ጋር በመሆን እንጠይቃለን።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0