ስፑትኒክ አድሏዊ ከሆኑት የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በተለየ እውነትን በማቅረቡ የአፍሪካውያንን እምነት አግኝቷል - የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
20:34 30.10.2026 (የተሻሻለ: 20:44 30.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ስፑትኒክ አድሏዊ ከሆኑት የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን በተለየ እውነትን በማቅረቡ የአፍሪካውያንን እምነት አግኝቷል - የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሰዎች እውነቱን ለማወቅ እስከፈለጉ ድረስ የሩሲያ የመረጃ መድረኮች ተጨባጭ ሽፋን የሚሰጡ በመሆናቸው በአኀጉሪቱ ላይ የበለጠ ተቀባይነት እንደሚያገኙ ሞሂኤልዲን ሳሌም አህመድ ኢብራሂም ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።
በዲፕሎማቱ የተሰጡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
⭕ አፍሪካውያን አድሏዊ፣ ፖለቲካዊ እና በዜና ስርጭት ተዓማኒ ባልሆነው የምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን "ከፍተኛ ጉዳት" ደርሶባቸዋል።
⭕ ስፑትኒክ ስለ አኀጉሪቱ እውነተኛ ያልሆነ ምስል የሚያቀርቡ "አሳሳች ጣቢያዎችን" ለመመከት በአፍሪካ ያለውን ተደራሽነት ማስፋፋት ይኖርበታል።
⭕ ሚኒስትሩ ለተቋሙ ስኬት እንኳን አደረሳችሁ በማለት፣ በመሬት ላይ ድል ከተቀናጀና ዘላቂ ሰላም ከተረጋገጠ በኋላ ስፑትኒክ ሱዳንን እንዲጎበኝ ጥሪ አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
