ሩሲያ እና አፍሪካ በፍትሐዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተደራሽነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እና አላስፈላጊ አጠቃቀምን በመከላከል ላይ ተስማሙ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ እና አፍሪካ በፍትሐዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተደራሽነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እና አላስፈላጊ አጠቃቀምን በመከላከል ላይ ተስማሙ
ሩሲያ እና አፍሪካ በፍትሐዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተደራሽነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እና አላስፈላጊ አጠቃቀምን በመከላከል ላይ ተስማሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 30.10.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና አፍሪካ በፍትሐዊ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ተደራሽነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት እና አላስፈላጊ አጠቃቀምን በመከላከል ላይ ተስማሙ

ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን ለሲቪል አገልግሎት በማዋል ትብብር ለማድረግ የሚያስችል የጋራ መግለጫ ያፀደቁ ሲሆን፣ ቴክኖሎጂውን ለማልማት እና ለመጠቀም የሚያስችሉ የጋራ ቅደም ተከተሎችን አስቀምጠዋል።

በመግለጫው የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች፡-

🟠 ፍትሐዊ ተደራሽነት፦ ሁለቱም ወገኖች እውቀትን፣ የመረጃ ቋቶችን፣ የኮምፒውተር ማቀናበሪያ ኃይልን፣ ሶፍትዌሮችን እና ሃርድዌሮችን ጨምሮ ለሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕድገት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን እኩል እና አድሎ የሌለበትን ተደራሽነትን ይደግፋሉ።

🟠 የሀገር ውስጥ ሕግጋት፡ የሰው ሠራሽ አስተውሎት አልሚዎች እና አቅራቢዎች እውቀት አእምሮአዊ ንብረት ሕጎችን፣ የመረጃ ጥበቃን፣ የደንበኞችን መብት እና የመረጃ ደህንነት ደንቦችን ጨምሮ ቴክኖሎጂዎቻቸው በሚገበዩባቸው ሀገራት ሕጎች የመገዛት ግዴታ አለባቸው።

🟠 የጋራ መስፈርቶች፦ ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት ለሰው ሠራሽ አስተውሎት መስፈርቶች፣ ቴክኒካዊ ብቃቶች፣ ግልጽነት እና የስጋት አስተዳደር እንዲሁም ለፍትሐዊ የገበያ ተደራሽነት ተለዋዋጭእና አድልዎ የሌለባቸውን አቀራረቦች ይደግፋሉ።

🟠 አላስፈላጊ አጠቃቀምን መታገል፦ መግለጫው ሰው ሠራሽ አስተውሎትን የተሳሳቱ መረጃዎችን ለማሰራጨት፣ ወሳኝ የመሠረተ ልማት አውታሮችን ለማጥቃት እንዲሁም በኢኮኖሚ እና በሰዎች ደህንነት ላይ ጉዳት ለማድረስ አላስፈላጊ በሆነ መንገድ መጠቀምን በተመለከተ ያለውን ስጋት ገልጿል። ሁለቱም ወገኖች እነዚህን ስጋቶች ለመለየት እና ለመቀነስ ልምድ ለመለዋወጥ ተስማምተዋል።

🟠 በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተሰሩ ይዘቶችን መለየት፦ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የተሰሩ ይዘቶችን ለመለየት እና ምልክት ለማድረግ ሁለንተናዊ ደንቦችን እና ወጥ፣ ክፍት እንዲሁም አድልዎ የሌለባቸውን አቀራረቦች፣ በተለይም አውቶማቲክ የሆኑ አስተማማኝ የመለያ ዘዴዎችን ይጠይቃሉ።

🟠 የዲጂታል ልዩነትን መቀነስ፦ የሀገራትን የኤአይ ሉዓላዊ አቅም እና የቴክኖሎጂ ነፃነት ለማጠናከር የሚረዱ የጋራ ፕሮግራሞችን፣ የእውቀት ልውውጦችን እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን ያከብራሉ።

🟠 ሥራ እና ክህሎት፦ የሰው ሠራሽ አስተውሎት ዕድገት ምቹ የሥራ ሁኔታዎችን፣ ጥራት ያላቸውን ሥራዎች፣ እኩል ዕድሎችን እና ምርታማነትን መደገፍ አለበት። ቴክኖሎጂውን ሥራ ላይ ማዋል ከስልጠና፣ ከክህሎት ማሻሻያ፣ ከዲጂታል እውቀት እና ከሂሳዊ አስተሳሰብ ክህሎቶች ጋር ጎን ለጎን መሄድ አለበት።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0