ሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ የጋራ የአቋም መግለጫ - ቁልፍ ድንጋጌዎች
የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ በጋራ መግለጫ ፊርማ መጠናቀቁን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከጉባኤው በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።
ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት በሚከተሉት ጥቦች ላይ ተስማምተዋል ፦
🟠 የኢነርጂ ሉዓላዊነት እና ደህንነትን ማረጋገጥ።
🟠 ወረርሽኞችን እና ተላላፊ በሽታዎችን ለመዋጋት ያለውን ዝግጁነት ማጠናከር።
🟠 የዓለም አቀፍ የጦር መሣሪያዎች ቁጥጥር ሥርዓቶች በፖለቲካ ተፅዕኖ ሥር እንዳይወድቁ መከላከል::
🟠 ታሪክን የማዛባት እና ባዕድ ትርክቶችን የመጫን ሙከራዎችን መታገል።
🟠 ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋም፣ የዓለም የንግድ ድርጅት እና የዓለም ባንክን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ አስቸኳይ ማሻሻያ ማድረግ።
🟠 አሁን ያለውን የጂኦፖለቲካዊ እውነታ የሚያንፀባርቅ የተመድ የፀጥታዉ ምክር ቤት ማሻሻያ ማድረግ።
🟠 ያለበቂ ምክንያት የሲቪል መርከቦችን ማገድ፣ መያዝ ወይም ማሰርን ማውገዝ።
🟠 በቅኝ ግዛት ወቅት ለደረሱ ጉዳቶች ግምገማ ለማድረግ እና ካሳ ለማስከፈል የሚያስችሉ የሕግ ማዕቀፎችን መዘርጋት።
🟠 በጋራ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘቦችን አጠቃቀም ማስፋፋት።
🟠 የሽብርተኝነትን አደጋ ለመከላከል የሚደረገውን ትብብር ማጠናከር፤ ይህም አሸባሪዎች እንደ ድሮኖችን እና የኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ ያሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚጠቀሙበትን መንገድ መታገልን ያካትታል።
🟠 የአፍሪካ ግጭቶችን "ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ" በሚለው መርህ መሠረት መፍታት።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

