ሩሲያና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም እንሚይዙ ገለፁ
00:19 29.10.2026 (የተሻሻለ: 00:44 29.10.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም እንሚይዙ ገለፁ
ይህ የተገለጸው በሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን እና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መካከል በተካሄደ ውይይት ነው።
የስብሰባው ዋና ዋና ነጥቦች፦
ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት ወዳጃዊ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በ2027 የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤን በተሳካ ሁኔታ እንድታስተናግድ ፑቲን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር በኑክሌር ዘርፍ ያላትን ትብብር በተቀናጀ ሁኔታ ለማስቀጠል ትፈልጋለች። ፑቲንም ዐቢይ አሕመድ በድጋሚ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመመረጣቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አቅርበዋል።
በሩሲያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የንግድ ልውውጥ በእጅጉ መጨመሩን ፑቲን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ባላት ትብብር ደስተኛ እንደሆነች ገልጻለች።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

