- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የፓን-አፍሪካ የክፍያ እና ሴትልመንት ስርዓት (PAPSS)፣ የዶላር ጥገኛነት መቀነስ እና የኢትዮጵያ አህጉራዊ የንግድ ውህደት

የፓን-አፍሪካ የክፍያ እና ሴትልመንት ስርዓት (PAPSS)፣ የዶላር ጥገኛነት መቀነስ እና የኢትዮጵያ አህጉራዊ የንግድ ውህደት
ሰብስክራይብ

የፓን አፍሪካ የክፍያ እና ሴትልመንት ስርዓት ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ እና ከመላው አፍሪካ ጋር ያላትን የንግድ ግንኙነት ለማነቃቃት እና ለማሳደግ የሚያገለግል ትልቅ መሳሪያ ነው። ሀገራት በራሳቸው የሀገር ውስጥ ገንዘብ በቀጥታ እንዲገበያዩ በማድረግ በዶላር ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥገኛነት ይቀንሳል፤ የውጭ ወኪል ባንኮች ሂደት ላይ የሚወጣውን ጊዜ እና ወጪ በማስቀረት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ጫናን በከፊል ያቃልላል። ይሁን እንጂ የብር አቅም የሚጠናከረው በዋናነት በሀገሪቱ ኤክስፖርት አቅም፣ በምርት ጥራት እና በማክሮ ኢኮኖሚ መረጋጋት ላይ ተመስርቶ ነው፤" ሲሉ የቢዝነስ እና ኢንቨስትመንት አማካሪ ሙስጠፋ አብደላ ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ የፓን-አፍሪካ የክፍያ እና ሴትልመንት ስርዓት (PAPSS) ለአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና(AfCFTA) ስኬት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የቴክኖሎጂና የፋይናንስ ዝግጁነት፣ እንዲሁም አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ውህደትን እውን ለማድረግ የሚረዱ የትብብር ማዕቀፎችን በጥልቀት ተወያይተናል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን የኤክስፖርት አቅም በማሳደግና የጋራ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ረገድ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች ተመልክተናል።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer– Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0