ምዕራባውያን መሩ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት በአፍሪካና ሩሲያ መካከል ያለውን ንግድ እያደናቀፈ ነው - የኤርትራ ፕሬዚዳንት

ሰብስክራይብ

ምዕራባውያን መሩ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት በአፍሪካና ሩሲያ መካከል ያለውን ንግድ እያደናቀፈ ነው - የኤርትራ ፕሬዚዳንት

በሩሲያና በአፍሪካ መካከል ተጨባጭ የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የኢኮኖሚ ፕሮጀክቶች ወደፊት ሊራመዱ የሚችሉት መሠረታዊ ዓለም አቀፍ እንቅፋቶች ሲፈቱ ብቻ እንደሆነ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳይስ አፈወርቂ ተናግረዋል።

በሞስኮ ከተካሄደው 3ኛው የሩሲያ–አፍሪካ ጉባኤ ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ በሰጡት ልዩ ቃለ ምልልስ፤ በምዕራባውያን የሚመራው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓትና “ሩሲያን የመገደብ ፖሊሲ” በቅድሚያ መፍትሄ እንደሚያሻቸው ገልጸዋል።

የፕሬዚዳንቱ ቁልፍ ነጥቦች፦

ሥርዓታዊ እንቅፋቶች፦ “እንቅፋት እየሆኑ ያሉትን ጉዳዮች መፍታት ያስፈልጋል። የትኛውንም አጋርነት ለመደገፍ የሚያስችል የፋይናንስ ሥርዓት አለን?” ሲሉ ጠይቀዋል።

የዜሮ ድምር ፖለቲካን ውድቅ ማድረግ፦ የአሁኑን ዓለም አቀፍ ሥርዓት አንዱ የሚያተርፍበት ሌላው የሚከስርበት የ “ዜሮ ድምር” ሥርዓት ሲሉ የተቹት ፕሬዚዳንቱ፤ ሩሲያ ከሁለት እስከ ሦስት ዓመታት ውስጥ ፍትሐዊ የንግድ ግንኙነቶችን መመሥረት ትችላለች ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ሕጎችን መበየን፦ ከሩሲያ ጋር ሊመሠረት ለሚችለው የኢኮኖሚ አጋርነት መሠረታዊ ቅድመ ሁኔታዎችን ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ንግድ በዶላር፣ በዩሮ ወይስ በሩብል ነው የሚካሄደው ሲሉ ጠይቀው፤ ከሁሉም በፊት የንግድ ሕጎች መገለጽና መሟላት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0