ሩሲያ ከምዕራባውያን ቁጥጥር ውጭ የሚሠሩ የክፍያ ሥርዓቶችን አስተዋወቀች

ሰብስክራይብ

ሩሲያ ከምዕራባውያን ቁጥጥር ውጭ የሚሠሩ የክፍያ ሥርዓቶችን አስተዋወቀች

የሩሲያ ባንኮችና የውጭ ሀገራት አጋሮቻቸው በምዕራባውያን የፋይናንስ ሥርዓቶች ላይ ሳይመረኮዙ ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን እየፈጸሙ መሆኑን የክሬምሊን ምክትል የጽሕፈት ቤት ኃላፊ ማክሲም ኦሬሽኪን ሩሲያ–አፍሪካ መድረክ ለፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገልጸዋል።

“ከአምስት ዓመት በፊ እንደ አብዛኞቹ ሀገራት ሁሉ ለውጭ ንግዳችን በዋናነት በዶላርና በዩሮ እንመረኮዝ ነበር” ያሉት ኦሬሽኪን፤ የሩሲያ ባንኮችና የውጭ ሀገራት አጋሮቻቸው አሁን ዲጂታል ቴክኖሎጂዎችንና ከባንክ ውጭ የሆኑ የፋይናንስ ተቋማትን በመጠቀም ዓለም አቀፍ ክፍያዎችን እየፈጸሙ እንደሆነ አብራርተዋል።

የሩሲያ የፋይናንስ ሚኒስትር አንቶን ሲሉአኖቭ በበኩላቸው፤ ኤ7 የተባለው የሩሲያ ኩባንያ በአፍሪካ የድንበር ተሻጋሪ የክፍያ አገልግሎት ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። አገልግሎቱ በአንድ ጠቅታ እንደሚፈጸምና የግብይት ክፍያውም 0.3% ብቻ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

ፑቲን በበኩላቸው፤ “ማንም ከሥርዓቱ ሊያቋርጣችሁ አይችልም። ከቴክኖሎጂ አንጻር እንዲህ ያሉ ክፍያዎችን ማገድ የማይቻል ነው” በማለት፤ ሥርዓቱ ሉዓላዊና ግልጽ መሆኑን እንዲሁም በልማዳዊና በዲጂታል መገበያያዎች መካከል ፈጣን ልውውጥ ማድረግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0