ሩሲያና ታንዛኒያ የጋራ የጠፈር ምርምር ፕሮግራም ጀመሩ
16:22 28.10.2026 (የተሻሻለ: 16:33 28.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ሩሲያና ታንዛኒያ የጋራ የጠፈር ምርምር ፕሮግራም ጀመሩ
የሩሲያ የጠፈር ምርምር ድርጅት ሮስኮስሞስ ዋና ዳይሬክተር ዲሚትሪ ባካኖቭ ከታንዛኒያ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ቋሚ ጸሐፊ ሙሃመድ ካሚስ አብዱላ ጋር የስትራቴጂክ አጋርነትና ትብብር ስምምነት ፈርመዋል።
ሩሲያ በታንዛኒያ የጠፈር ኢንዱስትሪ ለመመሥረት የሚያስፈልጉ መሠረተ ልማቶችን በማዘጋጀት ድጋፍ ታደርጋለች። በተጨማሪም በሀገሪቱ የጠፈር ኤጀንሲ ለማቋቋም የምክር ድጋፍ ትሰጣለች።
ሁለቱ ሀገራት በሕዋ ዘርፍ የሚሠሩ ባለሙያዎችን በማሠልጠን ረገድ በጋራ ለመሥራትና ልምድ ለመለዋወጥ ተስማምተዋል።
ሩሲያ በመጋቢት ወር የመጀመሪያውን የታንዛኒያ የምድር ገጽታ ቃኝ ሳተላይት ወደ ሕዋ ታመጥቃለች።
ሁለቱ ወገኖች በሁሉም የትብብር ዘርፎች የሥራ ሂደቱን በተደራጀ መልኩ ለማስኬድ የጋራ የሥራ ቡድኖችንና የትግበራ ፍኖተ ካርታዎችን ለማዘጋጀት ተስማምተዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X