ፑቲን በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ የአፍሪካን እያደገ የመጣ ኃይል በማወደስ፤ ኒዮ-ኮሎኒያሊዝምን ውድቅ አደረጉ
15:27 28.10.2026 (የተሻሻለ: 16:34 28.10.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ፑቲን በሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ የአፍሪካን እያደገ የመጣ ኃይል በማወደስ፤ ኒዮ-ኮሎኒያሊዝምን ውድቅ አደረጉ
በጉባኤው መክፈቻ በቭላድሚር ፑቲን የተሰጡ ዋና ዋና መግለጫዎች፦
የጠናከረው የአፍሪካ ድምፅ
ባለብዙ-ወገን ዓለም በማይቀለበስ አካሄድ እውን እየሆነ ነው። ቢሆንም ግን "በሌሎች ኪሳራ የበለፀጉ" ልማደኛ ሀገራት አካሄዱን ይቃወሙታል።
የአፍሪካ አኀጉር በዓለም መድረክ ያለው ተፅዕኖ እና ተቀባይነት እየጨመረ ነው።
በዓለም አቀፍ ድርጅቶች፤ በተለይም በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና በዓለም ባንክ ውሳኔ አሰጣጥ ውስጥ የአፍሪካን ሚና ማጠናከር አስፈላጊ ነው።
ማዕቀቦች እና ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም
ሞስኮ የአፍሪካ ሀገራት ምዕራባውያን በሩሲያ ላይ የጣሉትን ማዕቀብ ውድቅ በማድረግ የያዙትን ጽኑ አቋም ታደንቃለች።
የታሪፍ ጦርነቶች እና ሕገ-ወጥ ማዕቀቦች የኒዮ-ኮሎኒያሊዝም መሣሪያዎች ናቸው።
ብሪክስ፣ ፋይናንስ እና የገንዘብ ሉዓላዊነት
በአምስት ዓመታት ውስጥ ብሪክስ ከዓለም ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ከ40 በመቶ በላይ ሲያመነጨ የቡድን 7 ድርሻ ግን ከ30 መቶ በታች ነው።
የአፍሪካ ሀገራት አሁንም በምዕራባውያን የፋይናንስ ስርዓቶች ላይ ጥገኛ ናቸው፤ ይህም ሉዓላዊነታቸውን ይገድበዋል።
ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት በሀገር ውስጥ ገንዘብ የሚፈጸም የክፍያ ስርዓት መዘርጋት አለባቸው።
የኢኮኖሚ ትብብር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር
በሩሲያ እና በአፍሪካ መካከል ያለው የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነት በጫና እና ማዕቀቦች ውስጥ እያደገ ነው።
የሩሲያ ኩባንያዎች በአፍሪካ የሚያካሂዱትን እንቅስቃሴ በስኬት እያከናወኑ ይገኛሉ፤ አዳዲስ ኩባንያዎችም ወደ አኅጉሪቷ እየገቡ ነው።
የሩሲያ ድርጅቶች በአፍሪካ ውስጥ ብዝበዛ ወይም ቅኝ ግዛታዊ ምዝበራ አያካሂዱም፤ ይልቁንም ለአኅጉሪቱ ዕድገት ይሠራሉ።
ሩሲያ የከፍተኛ ቴክኖሎጂ መፍትሔዎቿን ለአፍሪካ ሀገራት ለማስተላለፍ ዝግጁ ነች።
የምግብ ዋስትና
ሩሲያ ለአፍሪካ እጅግ አስተማማኝ የምግብ ዋስትና አቅራቢ ናት፤ ከ40 በላይ ሀገራት የሩሲያን እህል እና ማዳበሪያ ያገኛሉ። ሞስኮ ስርጭቷን የበለጠ ለማሳደግ ዝግጁ ነች።
ኢነርጂ
ሩሲያ በ16 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከ30 በላይ የኢነርጂ ፕሮጀክቶች ትግበራ ላይ እየተሳተፈች ይገኛለች።
ትምህርት እና ጤና
እ.ኤ.አ ከ2020 ጀምሮ በሩሲያ ውስጥ የተማሩ የአፍሪካ ተማሪዎች ቁጥር በ1.5 እጥፍ አድጓል።
ሩሲያ ውጤታማ የሆኑ መድኃኒቶችንና ክትባቶችን በአፍሪካ ውስጥ ለማምረት አቅዳለች።
በእንግሊዘኛ ያንብቡ
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X