- Sputnik አፍሪካ, 1920
Continental Drift
በአፍሪካ ቅርፅ እየቀየሩ ያሉትን እንደዚሁም የደቡባዊውን ዓለም ክፍል ሚና በአዲስ መልክ እየገለጹ ያሉትን ስር ነቀል ለውጦች የሚቃኝ ፕሮግራም ነው። ትዕይንቱ ፖሊሲዎች፣ ገበያዎች እና ፈጠራዎች ከዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር እንዴት እንደሚገናኙ በመመርመር በእውነታ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን እና ትክክለኛ የአፍሪካ አመለካከቶችን ያቀርባል።

የሩሲያ እና አፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት፡ ከፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል እስከ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት

የሩሲያ እና አፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት፡ ከፀረ-ቅኝ ግዛት ትግል እስከ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት
ሰብስክራይብ
የሩሲያ እና አፍሪካ ታሪካዊ ግንኙነት በፀረ-ቅኝ ግዛት ትግሎች፣ በዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ድጋፎች እንዲሁም በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ባለብዙ-ሀክ ሥርዓትን የማረጋገጥ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂ ላይ የተመሠረተ ነው። የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን ዓለም አቀፍ የበላይነትን ለመቆጣጠር በሚደረግ ፉክክር የተሞላበት በነበረበት ወቅት፣ ሶቪየት ኅብረት (የሩሲያ) አፍሪካውያን ከምዕራባውያን ተጽዕኖ ነፃ እንዲወጡ ሰፊ ድጋፍ አድርጓል።
"የሩሲያ አፍሪካን ከምዕራባውያን የበላይነት ነፃ ለማውጣት ትልቅ ሚና ተጫውታለች፤ ይህ ደግሞ በእርግጥም የእነሱ የፖለቲካ ስትራቴጂ ነበረ። በራሽያ እና በምዕራባውያን ኃይሎች መካከል በፖለቲካ እና በዓለም ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ፉክክር ነበር፤ የምዕራባውያን ኃይሎች ሁሉንም ነገር ለመቆጣጠር ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው ሲሆን፣ አንድን አካል ብቻ ያማከለ (Unipolar) ሥርዓት እንዲኖር ይፈልጋሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ራሽያ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓትን ትደግፋለች። ስለዚህም ከዚህ አንፃር ራሽያ በቀዝቃዛው ጦርነት ፖለቲካ ወቅት አፍሪካውያንን ደግፋለች። እንደምናውቀው፣ ብዙ አፍሪካውያን አገራት ነፃነታቸውን ያወጁት በራሽያ ድጋፍ ነው። ራሽያ እንደ ደቡብ አፍሪካ፣ ናሚቢያ፣ አንጎላ እና መሰል አፍሪካዊ አገራት የውትድርና እና የመረጃ ድጋፎችን አድርጋለች።"ሲሉ በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ ከፍተኛ መምህር በላይ በየነ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
በዛሬው የኮንቲነንታል ድሪፍት ዝግጅታችን፣ የራሽያ እና አፍሪካን ታሪካዊ ትስስር፣ የቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን የነፃነት ትግሎች ድጋፍ እንዲሁም ራሽያ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓትን ለመፍጠር የምታደርገውን ፖለቲካዊ ስቃሴ እንፈትሻለን። ለዚህም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና የፖለቲካ ታሪክ ከፍተኛ መምህር ከበላይ በየነ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እናቀርባለን።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0