- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

ሩሲያ እና አፍሪካ፣ ባለብዙ መልክ የዓለምን ስረዓትን የመገንባት ጉዞ

ሩሲያ እና አፍሪካ፣ ባለብዙ መልክ የዓለምን ስረዓትን የመገንባት ጉዞ
ሰብስክራይብ
እ.ኤ.አ. ጥቅምት መጨረሻ 2026 የሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ወንበር እንድታገኝ፣ በዓለም አቀፍ ማሻሻያዎች እና በሰላማዊ ኒውክሌር ትብብር ላይ ይመክራል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን፣ በተለይም የፀጥታው ምክር ቤትን ማሻሻል የታዳጊ ሀገራት የዘወትር አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል። እንደውም የአሁኑ ጉባኤ አፍሪካን ጨምሮ የታዳጊ ሀገራት ተወካዮች በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ አባል የሚሆኑበትን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የማሻሻያ ውሳኔ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ጠንካራ ግፊት ያደርጋል" ሲሉ

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

የሦስተኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ለአፍሪካ ሀገራት፣ ለኢትዮጵያ፣ እንዲሁም የዓለምን የኃይል ሚዛን ይበልጥ ፍትሐዊ ወደሆነ አቅጣጫ ለማሸጋገር ለሚደረገው ሰፊ ትግል ያለው ትርጉም ምድነው? በዛሬው የድረም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን ከእንግዶቻችን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባል እና ዘላለም ተፈራ (ዶ/ር)፦ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም የኢትዮጵያ ታሪክና ማኅበረሰቦች ጥናት ማዕከል መሪ ጋር በመሆን ይህንን ጉዳይ እንቃኛለን።

🔊 ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በእንግሊዘኛ ቋንቋ የቀረበውን ፕሮግራም ያዳምጡ:
ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0