- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

ራስን የማስተዳደርና የሥነ-ምግባር ነፃነት ለአፍሪካ ህልውና

ራስን የማስተዳደርና የሥነ-ምግባር ነፃነት ለአፍሪካ ህልውና
ሰብስክራይብ

''እውነተኛ ሥነ-ምግባር ከውጭ አገር ተሸክፎ የሚመጣ ሸቀጥ ሳይሆን፣ ከህዝብ ታሪክ፣ መንፈሳዊ እሴትና አኗኗር የሚቀዳ ነው። አፍሪካውያን የምዕራባውያንን ግለሰብ-ተኮር እይታ አውርደው ከመቀበል ይልቅ የራሳቸውን ማህበራዊና ባህላዊ የሞራል መሰረት ካልጠበቁ የባህል ወረራ ሰለባ ይሆናሉ::” ሲሉ የኢትዮጵያ የስነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት አባ መዝገቡ ካሳ(ዶ/ር) ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮች በሚዳሰሱበት የዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም በክፍል አንድ: የሥነ-ምግባር ሉዓላዊነት፡ ዓለም አቀፍ እሴቶች እና የአካባቢ ማንነት በሚል ርዕስ አፍሪካ የሞራል መሰረቷን እንዴት መጠበቅ ትችላለች በሚለው ላይ እንመክራለን። አባ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር) ፣ የኢትዮጵያ የስነ-ምግባር ማዕከል ፕሬዝዳንት እና የቅድስት ሥላሴ ቴዎሎጂ ዩኒቨርሲቲ መምህር ደግሞ ዕይታቸውን ያጋሩናል።

በክፍል ሁለት: የአፍሪካ ሀገራት ከውጭ ተፅዕኖ ነፃ የሆነ እና ገለልተኛ ፖሊሲን ለመከተል የሚያደርጉት ጥረት በሚል ርዕስ አህጉሪቱ ከኒዮ-ኮሎኒያሊዝም እና ከጂኦ-ፖለቲካዊ ጫናዎች ወጥታ ስትራቴጂካዊ ነፃነቷን እንዴት ማረጋገጥ እንዳለባት እንቃኛለን። አብዲ ዘነበ (ዶ/ር) ፣ በኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ደግሞ ሀሳባቸውን ያካፍሉናል።

ሙሉ መረጃዉን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0