- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የትራንስ-አፍሪካ የንግድ ኮሪደሮች እና የብሔራዊ የአግሮ-ኢኮሎጂ ስትራቴጂ ፋይዳ

የትራንስ-አፍሪካ የንግድ ኮሪደሮች እና የብሔራዊ የአግሮ-ኢኮሎጂ ስትራቴጂ ፋይዳ
ሰብስክራይብ

''የአህጉሪቱን የትራንስፖርት መረብ ከቀደመው የጥሬ ዕቃ መመዝበሪያነት አዙሪት አውጥቶ ከተሞቻችንን እርስ በርስ ወደሚያገናኝ የንግድ መስመር መለወጥ የኢኮኖሚ ነፃነት ማረጋገጫ ነው፤ ይህም ከባዕዳን የቴክኖሎጂ ጥገኝነት ለመላቀቅና በራስ አቅም ላይ የተመሠረተ የድንበር ተሻጋሪ ክፍያን ለመዘርጋት ግንባር ቀደም ምሰሶ ሆኗል'' ሲሉ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን መዋቅር ባለሙያውና የፖሊሲ አማካሪው ኬልቪን ጂራጂ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፖድካስት የመጀመሪያ ክፍል፤ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናን ውጤታማ ለማድረግ የዲጂታል መረጃ መስመሮችን፣ የተቀናጁ የድንበር ማቋረጫ የክፍያ ሥርዓቶችን እና የልዩ ኢኮኖሚ ቀጠናዎችን አጠቃቀም በምን መልኩ መቅረጽ እንደሚቻል እንቃኛለን። በሁለተኛው የፕሮግራማችን ክፍል ደግሞ፣ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የኬሚካል ግብዓቶች በአፈር ጤና ላይ እያደረሱት ያለውን አደጋ በመጋፈጥ፣ አዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የአግሮ-ኢኮሎጂ ስትራቴጂ ፍጹም የምግብ እና የአመጋገብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያለውን ሚና እንፈትሻለን። ዘመን ተሻጋሪ የግብርና ዕውቀቶችን ከሳይንሳዊ ምርምር ጋር በማቀናጀት ራሱን የቻለ አህጉራዊ ምርታማነትን መገንባት ስለሚቻልበት ሁኔታ ኢትዮጵያ ዘላቂ ስርዓተ-ምግብና ስነ-ምህዳራዊ ግብርና ሕብረት ዋና ዳይሬክተር ባዩሽ ፀጋዬ (ዶ/ር) እና ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና ተመራማሪ ፈለቀ ወልደየስ (ዶ/ር) ጋር ሰፊ ቆይታ አድርገናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0