- Sputnik አፍሪካ, 1920
Drum of Changes
ከጥንታዊ የስልጣኔ ምድሮች እስከ ዘመናዊ ከተሞች ልብ፣ በአፍሪካ አዲስ ጥሪ እየተስተጋባ ይገኛል። አፍሪካ የዓለምን የወደፊት ሁኔታ የምትቀርጽ ቸል ልትባል የማይገባት ኃይል ሆና እያደገች ነው። ለአስርት ዓመታት አፍሪካ የምትናገር፣ ነገር ግን የማትደመጥ ሆና ቆይታለች። ዛሬ ግን ጥሪው ግልፅ ነው። አፍሪካ ከዓለም የኃይል ማዕድ የሚገባትን ትክክለኛ ቦታ ትጠይቃለች። ይህ ፕሮግራምም ከአፍሪካ የሚስተጋቡ የለውጥ ድምፆችን በልካቸው ወደ አድማጭ ተመልካቾቹ ያደርሳል።

የደቡብ ዓለም ትብብር ለዓለም ሥርዓት መለወጥ

የደቡብ ዓለም ትብብር ለዓለም ሥርዓት መለወጥ
ሰብስክራይብ
በ15 የአፍሪካ ሀገራት በተደረገ ጥናት፣ ከዜናዎች አንድ ሶስተኛው ከውጭ ምንጮች የተገኙ ሲሆን፣ አራተኛውን ድርሻ ዋና ዋናዎቹ የምዕራባውያን የዜና ኤጀንሲዎች ይዘዋል። ከእነዚህ ዘገባዎች 81 በመቶ ያህሉ በችግሮች ላይ፣ 13 በመቶው ደግሞ በግጭትና በአመፅ ላይ ያተኮሩ ናቸው።

“ነባሩ የዓለም ሥርዓት ግሎባል ሳውዝ [የደቡቡ ዓለም] ጥሬ ዕቃ አቅርቦ የምዕራባውያኑን ጎተራ ከመሙላት ባለፈ፣ እሴት ጨምሮ እንዳያመርት መዋቅራዊ ጫና ያደርግበታል። መገናኛ ብዙሀን ደግሞ ይህንኑ ኢፍትሃዊ ትርክት ማስፈጸሚያ መሣሪያ ሆኖው ያገለግላሉ። በመሆኑም ይህንን አካሄድ አፍሪካ የራሷን የመገናኛ ብዙሃን አቅም መገንባት ወሳኝ የትግል ግንባሯ ይሆናል” ሲሉ ሐብታሙ ግርማ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ምርምር ኮንሰርቲየም ተመራማሪና በኢባዳን ዩኒቨርሲቲ የኢነርጂ ኢኮኖሚክስ ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናገሩ።

የግሎባል ሳውዝን መሠረታዊ ገጽታዎች፣ የምዕራባውያንን ኢፍትሃዊ አሰራር እና የብሪክስንና የሻንጋይ ድርጅቶችን ስትራቴጂካዊ ሚና በምንቃኝበት በዛሬው የድራም ኦቭ ቼንጅስ ዝግጅታችን፤ በአፍሪካ ኢኮኖሚ ምርምር ኮንሰርቲየም ተመራማሪና በኢባዳን ዩኒቨርሲቲ የኢነርጂ ኢኮኖሚክስ ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ ሐብታሙ ግርማን እንግዳ አድርገናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ Apple Podcasts – Deezer – Afripods – Spotify – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0