- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

በወጣቶች ተሳትፎ የተገነባ የህዝብ ልማት፦ የአህጉራዊ ንቅናቄ እና የራስን ችግር በራስ አቅም የመፍታት ስትራቴጂ

በወጣቶች ተሳትፎ የተገነባ የህዝብ ልማት፦ የአህጉራዊ ንቅናቄ እና የራስን ችግር በራስ አቅም የመፍታት ስትራቴጂ
ሰብስክራይብ

"ከ11 አፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ በጎ ፈቃደኞችን በየዓመቱ በመሰብሰብ በኢትዮጵያ ውስጥ መጥተው እንዲሰሩ እናደርጋለን፤ ከኛም ሀገር ያሉ በጎ ፈቃደኞችን ወደ ሌሎች አፍሪካ ሀገራት እንልካለን። ይህ ልውውጥ አፍሪካዊ አንድነትን እና መተሳሰርን እውን በማድረግ፣ ችግሮቻችንን በጋራ መፍታት እንደሚቻል በተግባር የሚያሳይ ነው፤" ሲሉ የወጣቶች ልማት ተሟጋች ሴና ኤቢሳ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ፕሮግራማችን፤ ከ18 እስከ 29 ዓመት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ጋና፣ ጋምቢያ እና በሌሎች የአህጉሪቱ ሀገራት ገጠራማ ቀበሌዎች በመሰማራት ሰብአዊነትን ማዕከል ያደረጉ ስራዎች እና የማህበራዊ ካርታ ስልቶችን በመጠቀም የህዝብን ልማት እንዴት እያረጋገጡ እንደሚገኙ በጥልቀት ተወያይተናል። እንዲሁም አህጉራዊ የወጣቶች የልውውጥ ፕሮግራሞች አፍሪካዊ ትስስርን ለማጠናከር ያላቸውን ሚና ተመልክተናል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0