- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

ከአየር ንብረት ፍትህ እስከ ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የአየር ጥራት፣ የታዳሽ ኃይል ሽግግር እና የሀገር ውስጥ የፈጠራ አቅም

ከአየር ንብረት ፍትህ እስከ ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካ የአየር ጥራት፣ የታዳሽ ኃይል ሽግግር እና የሀገር ውስጥ የፈጠራ አቅም
ሰብስክራይብ

''አፍሪካ ለአለም አቀፍ የካርቦን ልቀት የምታበረክተው አስተዋፅኦ ከ3 እስከ 4 በመቶ ብቻ ሆኖ ሳለ፣ የፋይናንስ ድጋፍ በብድር መልክ መቅረቡ አግባብ አይደለም፤ ፋይናንሱ በስጦታና በካርቦን ካሳ መልክ መምጣት አለበት። በተጨማሪም ከውጭ ሀገር የሚገዙ ውድ የአየር ጥራት መቆጣጠሪያ መሳሪያዎችን በሀገር ውስጥ በምናበለጽጋቸው የራሳችን ቴክኖሎጂዎችና ሶፍትዌሮች በመተካት የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነታችንን ማረጋገጥ አለብን፤'' ሲሉ በሲ40 ሲቲስ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የአየር ጥራት ቴክኒክ አማካሪ አቶ ጥበቡ አሰፋ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ዝግጅታችን፤ በአፍሪካ የአየር ንብረት ፍትህና የታሪካዊ ኃላፊነት መርህ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የልቀት ቅነሳ ዕቅድና የካርቦን ንግድ ዝግጅት፣ ተቋማት ከናፍጣ ጄነሬተር ወደ ፀሐይ ኃይል የሚያደርጉት ሽግግር፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተገጣጠመው የ"አዲስ ኤርኔት" የአየር ጥራት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂና አህጉራዊ ፋይዳውን በሰፊው ዳስሰናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0