- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የሳይንስና የውሃ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካን የውሃ ደህንነት በራስ አቅም፣ ጥናትና ነፃ የምርምር ፋይናንስ ማረጋገጥ

የሳይንስና የውሃ ሉዓላዊነት፦ የአፍሪካን የውሃ ደህንነት በራስ አቅም፣ ጥናትና ነፃ የምርምር ፋይናንስ ማረጋገጥ
ሰብስክራይብ

''የአፍሪካን የውሃ ደህንነት ለማረጋገጥ ችግሩ የእውቀት ወይም የምርምር እጥረት ሳይሆን፣ በተመራማሪዎችና በፖሊሲ አውጪዎች መካከል ቋሚ የመገናኛ ድልድይ አለመኖሩ ነው። የውጭ ፋይናንስ ጥገኝነትን በመቀነስ፣ የአፍሪካውያንን ነባራዊ ሁኔታ እና አካባቢን ያገናዘቡ የራሳችንን ስታንዳርዶች መቅረጽ አለብን፤ የምርምር ውጤቶች በመደርደሪያ ላይ የሚቀሩበት ጊዜ ማብቃት አለበት፤'' ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ጤና ቶክሲኮሎጂ ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሰብለወርቅ መኮንን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ዝግጅታችን፤ በአዲስ አበባ የተካሄደው "የአፍሪካ የውሃ ደህንነት 2026" አህጉራዊ ጉባኤ፣ የከተማ ተፋሰሶችና የከባድ ብረቶች ብክለት በህዝብ ጤና ላይ የደቀነው ስጋት፣ "ከሳይንስ ወደ ፖሊሲ" ትስስር፣ ተፈጥሮን መሰረት ያደረጉ ማጣሪያዎች ፣ እንዲሁም የምርምር ፋይናንስ ነፃነት እና የአፍሪካ ተመራማሪዎች የመረጃ ባለቤትነት አህጉራዊ ፋይዳን በሰፊው ዳስሰናል።

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ሙሉ ፕሮግራሙን ይከታተሉ ፡

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0