- Sputnik አፍሪካ, 1920
Turning Africa Forward
በአህጉሪቱ ስልታዊ መነቃቃት ላይ ግልጽ እይታን የሚሰጥ በስፑትኒክ አፍሪካ እየተዘጋጀ የሚቀርብ ፕሮግራም ። ከዜናዎች ባሻገር፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ ጂኦፖለቲካ ውስጥ ያላትን እየተለወጠ የመጣ ሚና በጥልቀት ይተነትናል፤ የወደፊቱን የዓለም ሥርዓት በመቅረጽ ረገድ ያለውን አቅጣጫ በሰፊው ይዳስሳል።

የግብርና ሉዓላዊነት፣ የሀገር ውስጥ የእሴት ሰንሰለት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አብዮት እና የአፍሪካ የምግብ ነፃነት

የግብርና ሉዓላዊነት፣ የሀገር ውስጥ የእሴት ሰንሰለት፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አብዮት እና የአፍሪካ የምግብ ነፃነት
ሰብስክራይብ

አፍሪካ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ በምዕራባውያን የበጎ አድራጎት አሰራርና በምግብ እርዳታ ላይ ጥገኛ መሆን ማቆም አለባት፤ የምግብ ማምረት ሂደቱን፣ የግብርና ፖሊሲውን፣ የዘር ሀብቱንና ገበያውን ሙሉ በሙሉ በራሷ ቁጥጥር ስር የማዋል ሉዓላዊ መብቷን ማረጋገጥ ይኖርባታል። የውጭ አገራት ጥገኝነትና የጂኤምኦ (GMO) የዘር ኒዮ-ኮሎኒያሊዝም የሚያስከትሉትን የኢኮኖሚና አእምሮአዊ ባርነት ሰብረን፣ ሀገር በቀል እውቀቶችን ከዘመናዊ ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች ጋር በማጣመር በራሳችን አፈርና ዘር ራሳችንን መመገብ አለብን፤'' ሲሉ

የግብርና ኤክስቴንሽን ተመራማሪው ፕሮፌሰር ዳንኤል ተመስገን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

በዛሬው የተርኒንግ አፍሪካ ፎርዋርድ ዝግጅታችን፤ የዓለም አቀፍ ግጭቶች በምግብ ሰንሰለትና በማዳበሪያ ዋጋ ላይ ያሳደሩትን ጫና፣ በምግብ ዋስትና እና በምግብ ሉዓላዊነት መካከል ያለውን መሠረታዊ ልዩነት፣ የተቀናጁ የዲጂታል ግብርና መድረኮች እና አነስተኛ አርሶ አደሩን የማበቃት ሚና፣ የሀገር በቀል ዘሮች ጥበቃ እና በቅርቡ ይፋ የተደረገውን 'Ethio-Seed Hub' እና የማህበረሰብ የዘር ባንኮች ፋይዳ፣ እንዲሁም በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) በኩል አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለቶችን የመገንባት አስፈላጊነትን በሰፊው ዳስሰናል።

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Podcast Addict – Pocket Casts – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0