ሩሲያን አሰይጥኖ ማሳየት በዓለም ላይ አስተማማኝ ደህንነትን ሊፈጥር አይችልም - ባለሙያ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያን አሰይጥኖ ማሳየት በዓለም ላይ አስተማማኝ ደህንነትን ሊፈጥር አይችልም - ባለሙያ
ሩሲያን አሰይጥኖ ማሳየት በዓለም ላይ አስተማማኝ ደህንነትን ሊፈጥር አይችልም - ባለሙያ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያን አሰይጥኖ ማሳየት በዓለም ላይ አስተማማኝ ደህንነትን ሊፈጥር አይችልም - ባለሙያ

"በአሁኑ ወቅት በአውሮፓ በፍጥነት እያደገ የመጣው ‘የሩሲያ ስጋት ትርክት’ በአኅጉሪቱ የደህንነት መዋቅሮች ውስጥ እንደ ልማድ ሆኗል" ሲሉ የቱርክ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ባለሙያ ቱባ ቼቢ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቫልዳይ የውይይት ክለብ ንግግራቸው ላይ እንደጠቀሱት፣ ከአመክንዮአዊ አደጋዎች ትንተና ወደ ሀገራዊ ርዕዮተ-ዓለም መሸጋገር ለዲፕሎማሲ የሚሆነውን ቦታ ያጠፋዋል።

"ይህ በዓለም አቀፍ መስክ ውስጥ በጣም አደገኛው የልዩነት መስመር ነው" ሲሉ ቼቢ ተናግረዋል።

ቀጣናዊ ወይም ዓለም አቀፍ ቀውስን እስከ ጦርነት አፋፍ በማድረስ ተቃራኒው ወገን እጁን እስኪሰጥ የመጠበቅ 'አፋፍ ላይ የተንጠለጠለ ፖሊሲ' ዘላቂ የደህንነት መዋቅርን ፈጥሮ እንደማያውቅ ታሪክ ያሳያል ሲሉ ባለሙያዋ አክለዋል።

"ደህንነትን ማረጋገጥ የሚቻለው ተቃዋሚን በመደምሰስ ሳይሆን ተገቢ የሆኑ ተቋማዊ አሰራሮችን በመፍጠር ነው" ሲሉ አብራርተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0