ሩሲያ እና ቶጎ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ገበያዎች የሚያስገባ የትራንስፖርት ኮሪደር በመፍጠር ዙሪያ ተወያዩ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ እና ቶጎ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ገበያዎች የሚያስገባ የትራንስፖርት ኮሪደር በመፍጠር ዙሪያ ተወያዩ
ሩሲያ እና ቶጎ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ገበያዎች የሚያስገባ የትራንስፖርት ኮሪደር በመፍጠር ዙሪያ ተወያዩ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 02.10.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ቶጎ ወደ ምዕራብ አፍሪካ ገበያዎች የሚያስገባ የትራንስፖርት ኮሪደር በመፍጠር ዙሪያ ተወያዩ

የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች በተጨማሪም የቶጎን የውሃ እና የኢነርጂ ሃብት ሙሉ በሙሉ ለማልማት በሚያስችል አጠቃላይ የማስተር ፕላን ንድፍ ዙሪያ መምከራቸውን በኢነርጂ ሚኒስትሩ ሴርጌይ ፂቪሌቭ የሚመራው የሩሲያ-ቶጎ መንግስታት መካከል ኮሚሽን ስብሰባን ተከትሎ የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር ገልጿል።

ይህ የማስተር ፕላን ንድፍ የሚከተሉትን ያካትታል፦

▪ ዋና ዋና የውሃ ተጠቃሚዎችን መለየት፣

▪ ከተዛማጅ ዘርፎች ጋር የተያያዘ የውሃ ሚዛን ማዘጋጀት፣

▪ የመሰረተ-ልማት ማሻሻያዎችን ማካሄድ፣

▪ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ለመገንባት የሚያስችል ዝርዝር የድርጊት መርሃ-ግብር ማዘጋጀት።

በተጨማሪም ወገኖቹ በሚከተሉት ተቋማት መካከል የትብብር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፦

በሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የቁሳቁስ ባህል ታሪክ ኢንስቲትዩት እና በቶጎ ሪፐብሊክ የብሔራዊ ባህላዊ ቅርሶች ኮሚሽን መካከል፤

በሎሜ ዩኒቨርሲቲ፣ በሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ የአፍሪካ ጥናቶች ኢንስቲትዩት እና በኤ.ቪ. ቶፕቺዬቭ የፔትሮኬሚካል ሲንቴሲስ ኢንስቲትዩት መካከል የቀረቡ ስምምነቶች ናቸው።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0