- Sputnik አፍሪካ, 1920
The African Heights show
ወቅታዊ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች፣ አዳዲስ መረጃዎች እና በደቡባዊው ዓለም ሀገራት መካከል ጠንካራ ትስስር የሚፈጥሩ አበይት ክስተቶች የሚዳሰሱበት ፕሮግራም።

የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ፦ ለአፍሪካ ንግድና ኢኮኖሚ ያሏቸው እድሎች

የብሪክስ አዲሱ የልማት ባንክ፦ ለአፍሪካ ንግድና ኢኮኖሚ ያሏቸው እድሎች
ሰብስክራይብ
''ብሪክስ ሀገራት በራሳቸው ገንዘብ እንዲገበያዩ የሚያስችል ምጣኔ ሀብት እየዘረጋ ነው። በራሳቸው ገንዘብ መገበያየት ቻሉ ማለት በቀላሉ ምርታቸውን ወደ ዓለም ገበያ ማስገባት፣ ትርፍ ማግኘት፣ ከሌላ ሀገር ገንዘብ ጥገኝነት መውጣት መቻል፣ በፍጥነት መጓዝ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል'' ሲሉ አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ ኢኮኖሚስት ከአፍሪካ ሃይትስ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
የዓለም ኢኮኖሚ ስርዓት እየተለዋወጠ ባለበት ወቅት፣ ብሪክስ እና አዲሱ የልማት ባንክ በአፍሪካ ንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ኢኮኖሚ ላይ የሚኖራቸው ሚና ምን ይሆናል? በዛሬው የአፍሪካን ሃይትስ ፕሮግራም፣ በክፍል አንድ ብሪክስ እና አዲሱ የልማት ባንክ ለአፍሪካ ሀገራት የሚፈጥሯቸውን የንግድና የፋይናንስ ዕድሎች፣ እንዲሁም ሊኖሯቸው ስለሚችሉ ተፅዕኖዎች እንዳስሳለን። አሉላ ተክለብርሃን አዲሱ፣ ኢኮኖሚስት በዚህ ዙሪያ ያለውን ዕይታና ትንታኔ ያካፍሉናል።
በክፍል ሁለት የስነ-ጽሁፍ ሚና በማንነት እና በታሪክ ንቃተ-ህሊና ግንባታ ላይ ያለውን ሚና እንቃኛለን። የሻው ተሰማ፣ ደራሲ፣ ገጣሚ እና በኮተቤ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ጽሁፍ መምህር በዚህ ዙሪያ ያላቸውን ሃሳብና ትንታኔ ያካፍሉናል።

ሙሉውን መረጃ ለማግኘት ፕሮግራሙን ያዳምጡ:

ፖድካስታችንን በሌሎች አማራጮች ያድምጡ: Apple Podcasts – Deezer – Spotify – Afripods – Pocket Casts – Podcast Addict – CastBox
አዳዲስ ዜናዎች
0