ሩሲያ በዓለም ውቅያኖሶች ላይ ነፃ የመርከቦች ዝውውር እንዲኖር ትደግፋለች - ፑቲን

ሰብስክራይብ

ሩሲያ በዓለም ውቅያኖሶች ላይ ነፃ የመርከቦች ዝውውር እንዲኖር ትደግፋለች - ፑቲን

ሩሲያ ነፃ የመርከቦች (የባህር) ዝውውርን እንደምትደግፍ እና አዳዲስ የባህር ላይ ሕጎች አስፈላጊ ናቸው ብላ እንደማታምን የገለፁት ቭላድሚር

ፑቲን፣ ያሉትን ሕጎች ማክበር ብቻ በቂ መሆኑን ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ኪዬቭ በሲቪል የጭነት መርከቦች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ከ100 በላይ መርከቦች እንዲጎዱ አድርጋለች ሲሉ ወንጅለዋል። በአንጻሩ በጥቁር ባህር የሚገኙ የሩሲያ ኃይሎች ጥቃት ያደረሱት በወታደራዊ መርከቦች ላይ ብቻ እንደሆነ እና ስህተት 'በጭራሽ' እንደማይሰሩ ገልጸዋል።

ፑቲን አክለውም በሩሲያ የሲቪል የባህር ትራንስፖርት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶች የሚቀጥሉ ከሆነ ሞስኮ በማንኛውም የዓለም ውቅያኖስ ክፍል ላይ ተመጣጣኝ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስጠንቅቀዋል።

"ሩሲያ የማንንም መርከብ አትቀማም" ያሉት ፑቲን፣ የሞስኮ ተቃዋሚዎች ከእንዲህ ዓይነቱ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርበዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0