ታሪካችንን ከራሳችን ውጭ ሊናገርልን የሚችል አካል የለም - የኢኮዋስ ቱሪዝም አመራር
19:45 30.09.2026 (የተሻሻለ: 19:54 30.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ታሪካችንን ከራሳችን ውጭ ሊናገርልን የሚችል አካል የለም - የኢኮዋስ ቱሪዝም አመራር
ታሪካችንን ራሳችን ካልተናገርነው ሌላ ማንም አይናገርልንም ሲሉ የኢኮዋስ ቱሪዝም የግል ሴክተር ኮንፌደሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የጋና ሴቶች በቱሪዝም ውስጥ ማኅበር ፕሬዝዳንት ናንሲ ኳርተይ ሳም በኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ላይ “የዲጂታል ፈጠራ ለአካታች ቱሪዝም” በሚል ርዕስ በተካሄደ የፓናል ውይይት ላይ ነው፡፡
ናንሲ እንዳሉት በአፍሪካ የቅኝ ግዛት ዘምን ጠባሳውን ካሳረፈባቸው መስኮች አንዱ የቱሪዝም ሴክተሩ ነው፡፡ “ሆኖም አፍሪካውያን በተባበረ መንፈስ በመስራት ታሪክን መቀየር ይችላሉ፡፡” ብለዋል፡፡
“ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆኑት ከአፍሪካ ተፈንግለው ወደ ሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ደቡብ አመሪካ የተጋዙ ባሮች የተጓጓዙት በጋና የባሕር በር በኩል ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቷ “ይህ ታሪካችን ነው፤ እኛ ራሳችን ካልተናገርነው ሌላ ሊናገርልን የሚችል ኃይል የለም፡፡” ሲሉ በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
አፍሪካውያን ያላቸውን ከተፈጥሮ የተቆራኘ ሀብት ከቱሪዝም ፀጋዎች ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ ናንሲ ኳርተይ አመላክተዋል፡፡
"በአፍሪካ ሀገራት መካከል ነጻ ጉዞ እንዲኖር መሥራት አለብን፡፡ እንደ የአፍሪካ ሕብረት የመሳሰሉ አኅጉራዊ ተቋማትን ለዚህ ሥራችን ልንጠቀም ይገባል፡፡” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X