በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎች አፍሪካን በተዛባ ሁኔታ ተረድተዋታል፤ ይህን ምስል ለመቀየር ብሪክስ ጥሩ ዕድል ነው – የቱሪዝም ባለሙያ

ሰብስክራይብ

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎች አፍሪካን በተዛባ ሁኔታ ተረድተዋታል፤ ይህን ምስል ለመቀየር ብሪክስ ጥሩ ዕድል ነው – የቱሪዝም ባለሙያ  

 

አፍሪካ "ጨለማዋ አኅጉር" ተብላ በመሳሏ ዋናው ፈተናዋ ምስሏ እንደሆነ የኢትዮጵያ የቱሪስት አስጎብኚዎች ፕሬዝዳንት ፍፁም ገዛኸኝ ከኦሮሚያ የቱሪዝም ሳምንት ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል።

 

“ኢትዮጵያ እና አፍሪካ በባህል፣ በታሪክ እና በተፈጥሮ እጅግ የበለጸጉ ናቸው። [...] ነገር ግን አፍሪካ በአጠቃላይ ብዙም የታወቀች አይደለችም፡፡ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካታ ሰዎችም የተዛባ ሁኔታ ተረድተዋታል። ስለዚህ ለአፍሪካ ዋናው ፈተና ምስሏ ነው። ለብዙ ሰዎች አፍሪካ "ጨለማዋ አኅጉር" ናት ተብሎ ይታሰባል። ነገር ግን እሷ እንቁ አኅጉር ናት።”

 

ባለሙያው፣ የአፍሪካ ነባራዊ ሁኔታ ከሰሜን አሜሪካ፣ ከአውሮፓ፣ ከእስያ ወይም ከየትኛውም የዓለም ክፍል ፈጽሞ የተለየ እና ልዩ መሆኑን አብራርተዋል።

 

ብሪክስ እንዲቋቋም ካደረጉ በርካታ የተለያዩ ዓላማዎች አንዱ መሰል አሉታዊ ምሥሎችን መቀየር መሆኑ ያስታወሱት ፍፁም፤ ኢትዮጵያም የዚህ ማዕቀፍ አባል እንደመሆኗ ይህን ዕድል በቱሪዝም ኢንዱስትሪው ውስጥ ትጠቀምበታለች ብለዋል፡፡

 

“ይህንን የሰፋ ገበያ ማለትም የብሪክስ ገበያን (ቻይናውያንን፣ ሕንዳውያንን፣ ደቡብ አፍሪካውያንን፣ ብራዚላውያንን፣ እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን እና ሌሎች የብሪክስ አባላትን ሁሉ) ለመቅረብ በጣም ጥሩ አጋጣሚ ነው።” ሲሉ ባለሙያው ብሪክስ የአፍሪካን አሉታዊ ምስል መቀየሪያ ዕድል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የቱሪዝም ባለሙያው ያነሷቸውን ተጨማሪ ሐሳቦች ለማግኘት ቪዲዮውን ይመልከቱ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0