የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ መሠረት መጣል ለምስራቅ አፍሪካ ሉዓላዊነትን ትልቅ እርምጃ ነው - ዐቢይ አሕመድ

ሰብስክራይብ

የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ መሠረት መጣል ለምስራቅ አፍሪካ ሉዓላዊነትን ትልቅ እርምጃ ነው - ዐቢይ አሕመድ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ማለዳ፣ በኬንያ ላሙ ወደብ በ16 ቢሊዮን ዶላር የሚገነባው የዳንግቴ ምስራቅ አፍሪካ ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ ሥነ-ስርዓትን ከኬንያው ፕሬዝዳንት እና ከሌሎች የምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር ተካፍለዋል፡፡

 

ሁነቱን ተከትሎም ዐቢይ፣ "የላሙ የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ የመሠረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ሥነ-ስርዓት፤ የአፍሪካን የኢንዱስትሪ አቅም ለማሳደግ፣ መጠነ ሰፊ እድሎችን ለመፍጠር እና በመላው ምስራቅ አፍሪካ ለላቀ ኢኮኖሚያዊና የኢንዱስትሪ ሉዓላዊነትን መሠረት ለመጣል ትልቅ እርምጃ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሁነት ነው።" ሲሉ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ጽፈዋል፡፡

‎

‎በአኅጉሪቱ የሚገኙ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ባለሀብቶች እና ሥራ ፈጣሪዎች፤ በአፍሪካ ላይ ኢንቨስት ሊያደርጉ፣ አፍሪካ ባላት አቅምና የጋራ ጸጋ እምነት ሊኖራቸው እንዲሁም አኅጉራዊ መፃኢ እድልን የሚወስኑ ለውጥ አምጪ ፕሮጀክቶችን ሊገነቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

‎

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ "‎የአፍሪካን የወደፊት እጣ ፈንታ በጋራ ልንገነባው የተገባ ኃላፊነታችን ነው" ብለዋል፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0