ኢትዮጵያውያን አምራቾች 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ የሚገኝበትን የአፍሪካ ገበያ የሚደርሱበት አኅጉራዊ አሠራር ይዘረጋል – የፓፕስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
ኢትዮጵያውያን አምራቾች 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ የሚገኝበትን የአፍሪካ ገበያ የሚደርሱበት አኅጉራዊ አሠራር ይዘረጋል – የፓፕስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ
የፓን-አፍሪካን ክፍያ እና የገንዘብ ልውውጥ ሥርዓት (ፓፕስ*) ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማይክ ኦግባሉ ከኢቲ-ስዊች* ጋር የሚደረግ ቅንጅት ለኢትዮጵያ አነስተኛና መካከለኛ አምራቾች ከፍተኛ የገበያ እድል እንደሚፈጥር ከሁለተኛው የፋይናንስ ፎረም ጎን ለጎን ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።
“በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ የሚገኝ አነስተኛ የጫማ ወይም የቆዳ ውጤቶች አምራች፣ አሁን መላውን 1.4 ቢሊዮን የአፍሪካ ሕዝብ እንደራሱ ገበያ ማየት ይጀምራል። ከሌሎች ሀገራት የሚሰበስበው ክፍያ ወደ ሂሳቡ እንዴት ገቢ እንደሚሆን ሳይጨነቅ ንግዱን ማካሄድ ይችላል።” ብለዋል፡፡
አስፈጻሚው እንደገለጹት፣ አዲሱ አኅጉራዊ የክፍያ ሥርዓት አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ያላቸው አምራቾች የገንዘብ ዝውውር ሳያሳስባቸው ምርቶቻቸውን ለመላው አፍሪካውያን እንዲያቀርቡ የሚያስችል ነው፡፡
ከኢቲ-ስዊች ጋር በመቀናጀት በኢትዮጵያ ውስጥ የተከናወነውን መልካም ሥራ ወደ መላው አፍሪካ ማሳደግ እንደሚቻል ማይክ ኦግባሉ አስረድተዋል፡፡
*ኢቲ-ስዊች (EthSwitch) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሁሉንም የፋይናንስ ተቋማት (ባንኮች፣ አነስተኛ የፋይናንስ ተቋማት እና የዲጂታል ክፍያ ድርጅቶችን) እርስ በእርስ የሚያገናኝ የሀገር ውስጥ የክፍያ መሠረተ ልማት ነው።
*ፓፕስ (PAPSS) ደግሞ ይህንን የሀገር ውስጥ ሥርዓት ከአኅጉራዊው የክፍያ መረብ ጋር በማገናኘት የኢትዮጵያ ነጋዴዎች እና አጠቃላይ አፍሪካውያን በሀገር ውስጥ ገንዘባቸው በቀጥታ፣ በፍጥነትና ያለ እንግልት ንግድ እንዲያካሂዱ የሚያስችል ዓለም አቀፋዊ ድልድይ ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X