የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10 አዳዲስ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
16:53 30.09.2026 (የተሻሻለ: 16:54 30.09.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ 10 አዳዲስ የጭነት አውሮፕላኖችን ለመግዛት ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ስምምነት ተፈራረመ
የአየር መንገዱን የካርጎና ጭነት አገልግሎት አቅም በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያለመው የአውሮፕላኖቹ ግዢ ስምምነት ዛሬ በይፋ ተፈፅሟል።
ግዢው አሁን በስራ ላይ ያሉ 2 ቦይንግ 777 የጭነት አውሮፕላኖችን እና የወደፊቱን አዲስ ሞዴል 8 ቦይንግ 777-8ኤፍ አውሮፕላኖችን ያካተተ እንደሚሆን ተጠቅሷል።
አዲሶቹ አውሮፕላኖች አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ እያደገ የመጣውን የካርጎና ጭነት ትራንስፖርት ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችሉ እንደሚሆኑ ተጠቅሷል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X