የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ9 ዓመታት በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካዋ ደርባን ከተማ ዳግም በረራ ሊጀምር ነው
16:19 30.09.2026 (የተሻሻለ: 16:24 30.09.2026)
© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ9 ዓመታት በኋላ ወደ ደቡብ አፍሪካዋ ደርባን ከተማ ዳግም በረራ ሊጀምር ነው
አየር መንገዱ ከታህሳስ 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ደቡብ አፍሪካዋ የወደብ ከተማ የሚያደርገውን የቀጥታ የበረራ አገልግሎት በየዕለቱ ዳግም መስጠት እንደሚጀምር አስታውቋል።
በ2009 ዓ.ም ተቋርጦ የነበረ ይህ መስመር መከፈቱ፣ ደርባንን ከጆሃንስበርግ እና ኬፕታውን ቀጥሎ ሦስተኛዋ የአየር መንገዱ የደቡብ አፍሪካ መዳረሻው ያደርጋታል።
ቁልፍ መረጃዎች፦
ከታህሳስ 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘመናዊውን ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በመጠቀም በየዕለቱ የቀጥታ በረራ ይከናወናል።
በረራው በደርባን በሚገኘው የኪንግ ሻካ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት እና በአዲስ አበባ መካከል ይደረጋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደቡብ አፍሪካ ለ3 አስርት ዓመታት አገልግሎት የሰጠ ሲሆን፤ በ1985 ዓ.ም ወደ ጆሃንስበርግ፣ በ2007 ዓ.ም ደግሞ ወደ ኬፕታውን በረራ መጀመሩ ይታወሳል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X
